ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በርካቶች ተገደሉ
የዩክሬን አየር ኃይል ሩሲያ ካስወነጨፈቻቸው የተለያዩ 41 ሚሳይሎች ውስጥ 21 የሚሆኑትን መትቶ ማክሸፉን ገልጿል
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረሰችው መጠነሰፊ የአየር ድብደባ በርካቶች መገደላቸውን እና 50 የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናገሩ
ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በርካቶች ተገደሉ።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረሰችው መጠነሰፊ የአየር ድብደባ በርካቶች መገደላቸውን እና 50 የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናገሩ።
ሩሲያ ዛሬ ጠዋት የሀገሪቱን ትላልቅ ከተሞች-ኪቭ እና ካርካቭን ኢላማ ያደረገ የሚሳይል ጥቃት አድርሳለች።
ፖሊስ እና የአካባቢው አስተዳዳሪ እንደገለጹት በምስራቃዊቷ የዩክሬን ከተማ ካርኪቭ ላይ በደረሰ ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ እና 35 ሰዎች ቆስለዋል።
የከተማዋ ከንቲባ ኢሆር ትሬክሆቭ የነፍስ አድን ሰራተኞች ሰዎችን ለማትረፍ ፍርስራሾችን በመቆፈር ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የኪቭ ባለስልጣናት እንደተናገሩት በሶስት ከተሞች ላይ በደረስ ጥቃት 18 ሰዎች ቆስለዋል።
የዩክሬን አየር ኃይል ሩሲያ ካስወነጨፈቻቸው የተለያዩ አይነት 41 ሚሳይሎች ውስጥ 21 የሚሆኑትን መትቶ ማክሸፉን ገልጿል።
የዩክሬን ፕሬዝደንታዊ አስተዳዳር ኃላፊ አኔድሪ የርማክ በቴግራም ገጻቸው "እንዲህ አይነት ሽብር የሚቆመው በኃይል እንደሆነ አለም መረዳት አለበት" ብለዋል።
በተደጋጋሚ የሚሳይል ጥቃት የምታደርሰው ሩሲያ በዚህ ጥቃት ጉዳይ አስተያየት አልሰጠችም።
ዩክሬን ባለፈው እሁድ እለት በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባለችው የምስራቅ ዩክሬኗ ዶኔስክ ከተማ ጥቃት በማድረስ 27 ሰዎችን ገድላለች የሚል ክስ በሩሲያ ቀርቦባታል። ነገርግን ዩክሬን ጥቃቱን በማድረስ ሩሲያን ተጠያቂ አድርጋለች።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሁለት አመት ሊሞላው አንድ ወር ብቻ ይቀረዋል።