ሩሲያ በ158 ሚሳዔልና ድሮኖች ኪቭን ጨምሮ በዩክሬን ከተሞች ለይ ጥቃት ፈጸመች
ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በፈጸመችው ግዙፍ የሚሳዔል ጥቃት 30 ሰዎች ሞተዋል
የዩክሬን ጦር ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ እንዲህ አይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት አይተን አናውቅም ብሏል
ሩሲያ በ158 ሚሳዔልና ድሮኖች ኪቭን ጨምሮ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ለይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ።
ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በፈጸመችው ግዙፍ የሚሳዔል ጥቃት 30 ዩክሬናውያን ሞተዋል የተባለ ሲሆን፤ ከ160 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውም ተነግሯል።
ሩሲያ የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶቹን የዩክሬን ዋና ከተማ ኪቨን ጨምሮ በኦዴሳ፣ ደናይፕሮፕትሮስቮክ፣ ክሃርኪቭ እና ለቪቭ ከተሞች ላይ ነው የፈጸመችው።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ያላትን ሁሉንም አይነት የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማለች ያሉ ሲሆን፤ በጥቃቱም መኖሪያ ቤቶች አና የእናቶች ሆስፒታሎች መመታታቸውን አስታውቀዋል።
የዩክሬን አየር ኃይል በበኩሉ በአንድ ጊዜ በዚህ ልክ በርካታ ሚሳዔሎች ተተኩሰው አይቶ እንደማያውቅ አስታውቋ።
የኪየቭ የአየር መከላከያ በቅርብ ወራት ውስጥ በጣም ማሻሻ ተደርጎበት እንደነበረ እና ነገር ግን ትናንት አርብ ላይ ከሩሲያ የተተኮሱበት ሚሳዔሎች ከአቅሙ በላይ እንደሆኑበት ተነግሯል።
የዩክሬን አየር ኃይል ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፤ ሩሲያ ሃይፐረሶኑክ፣ ክሩዝ እና ባላስቲክ ሚሳዔሎችን ተጠቅማለች ያሉ ሲሆን፤ በተለይም በአየር ላይ ለማክሸፍ ከባድ የሆነውን X-22 ሚሳዔል መጠቀሟንም አስታውቀዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም “ይህን ያህል ኢላማዎች በአንድ ጊዜ ሲመቱ አይተን አናውቅም” ብለዋል።
የዩክሬን አየር ኃይል ሩሲያ ከተኮሰቻቸው 158 ሚሳዔሎች ና ድሮኖች መካከል ውስጥ 114 የሚሆኑት ተመትተው ወድቀዋል ብሏል።