ዩክሬን ሩሲያ በተኮሰችው የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃት በሽልማት ስነስርአት ላይ የነበሩ 20 ወታደሮች መገደላቸውን የሚየሳዩ ሪፖርቶች ውጥተዋል
ዩክሬን በወታደሮቿ ላይ የደረሰው ጥቃት እንዲመረመር ትዕዛዝ ሰጠች።
ዩክሬን ሩሲያ በተኮሰችው የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃት በሽልማት ስነስርአት ላይ የነበሩ 20 ወታደሮች መገደላቸውን የሚየሳዩ ሪፖርቶች ከወጡ በኋላ ጥቃቱ እንዲመረመር ትዕዛዝ መስጠቷን አስታውቃለች።
የ128ኛ ሰፖሬት ማውንቴን ብርጌድ አባላት በሆኑት ወታደሮች ላይ በደረሰው ጥቃት ሀዘናቸውን የገለጹት የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ሩስቴም ኡመሮቭ "ሙሉ ምርመራ" እንዲደረግ ማዘዛቸውን ተናግረዋል።
የዩክሬን ጦር በሰጠው ሌላ መግለጫ ሩሲያ የዛፖሬዥያ ግዛትን በኢስካንደር ሚሳይል አጥቅታለች ብሏል።
ጦሩ እንደገለጸው በጥቃቱ ወታደሮች ተገድዋል፤ የአካባቢው ነዋሪዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
ነገርግን ሚኒስትሩ ምን ያህል ወታደሮች እንደተገደሉ ግልጽ አላደረጉም።
ጦሩ ይህን መግለጫ ያወጣው በዛፖሬዥያ ግንባር የነበሩ ወቲደሮች "የአርቲለሪ" ቀን በሚከበርበት ወቅት በተዘጋጀው የሽልማት ስነስርአት ላይ 20 ወታደሮች መገደላቸውን የዩክሬን ማህበራዊ ሚዲያዎች እና ወታደራዊ ጸኃፊዎች መጻፋቸውን ተከትሎ ነው።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በእለታዊ ሪፖርቱ የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን የአጥቂ ብርጌድ ላይ ጥቃት በመሰንዘር 30 የሚደርሱ ወታደሮችን መግደሉን ገልጿል።
ሩሲያ እና ዩክሬን ብዙ ጊዜ በወታደሮቻቸው ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ዝቅ ስለሚያደርጉ ትክክለኛውን ቁጥር ማወቅ ያስቸግራል።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት 20 ወራትን አስቆጥሯል።