የካናዳ ገዢ ፓርቲ ማርክ ካነሪን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ
ከ9 አመታት በላይ ከናዳን የመሩት ጀስቲን ትሩዶ ከሀላፊነት ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ጦርነትን ለመፋለም ቃል ገብተዋል
የካናዳ ገዢ ፓርቲ ማርክ ካነሪን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ።
የካናዳ ገዥው ሊበራል ፓርቲ መሪ ለመሆን በተደረገው ውድድር የቀድሞው የማዕከላዊ ባንክ ሃላፊ ማርክ ካርኒ ማሸነፋቸውን እሁድ ዕለት የወጡ ይፋዊ ውጤቶች አሳይተዋል።
ካናዳ ከአሜሪካ ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ በምትገኘበት ጊዜ ወደ ስልጣን የሚመጡት ካርኒ በቅርቡ አጠቃላይ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ ሀገሪቱን እየመሩ ይቆያሉ፡፡
ለ9 አመታት ካናዳን የመሩት ጄስቲን ትሩዶ በህዝባቸው ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ የስራ መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ ፓርቲያቸው እሳቸውን ለመተካት ምርጫ አካሄዷል፡፡
የ59 አመቱ ካርኒ ከ152 ሺህ በታች የፓርቲ አባላት ድምጽ በሰጡበት ውድድር የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ክሪስቲያ ፍሪላንድን ለማሸነፍ 86 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል፡፡
ካርኒ ማሸነፋቸው ከተረጋጋጠ በኋላ ባደረጉት ትራምፕን በሚነቅፈው ንግግራቸው “ኢኮኖሚያችንን ለማዳከም የሚሞክር አንድ ሰው አለ፤ የካናዳ ሰራተኞችን፣ ቤተሰቦችን እና የንግድ ድርጅቶችን እያጠቃ ነው እንዲሳካለት ልንፈቅድለት አይገባም" ብለዋል፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ትራምፕ እያደረሱ የሚገኙትን ተጽዕኖ ለመቋቋም ከተለመደው የተለየ አካሄድን መከተል እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
ትራምፕ በካናዳ ላይ ለጣሉት የ25 በመቶ ታሪፍ የጀስቲን ትሩዶ አስተዳደር 30 ቢሊየን የካናዳ ዶላር ዋጋ ባላቸው የአሜሪካ ምርቶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ በማድረግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በካናዳ ታሪክ ምንም አይነት የፖለቲካ ልምድ ሳይኖራቸው ወደ ሀላፊነት የመጡት ካርኒ ሁለት የቡድን 7 አባል ሀገራት ካናዳ እና ብሪታንያ ብሔራዊ ባንኮች ገዢ ሆነው አገልግለዋል፡፡
የኢኮኖሚ ልምድ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ከትራምፕ ጋር በእኩል ቋንቋ ለመነጋገር ትክክለኛው ሰው እንደሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ካናዳን 51ኛ የአሜሪካ ግዛት አደርጋታለሁ የትራምፕ ንግርት እና ከታሪፍ ተጽዕኖ ጋር የሚጋፈጡት ካርኒ የፓርቲያቸውን ተቀባይነት ለማሳደግ በርካታ ስራ ይጠብቃቸዋል፡፡
በ2025 መጀመሪያ በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት በሁለተኛነት ከሚከተለው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ያለው ልዩነት ከ20 ነጥብ ያነሰ ነው፡፡
ሀገሪቱ በቅርቡ በምታደርገው ጠቅላላ ምርጫ ሊበራል ፓርቲ የ9 አመቱን ስልጣን ማስቀጠል የሚፈልግ ከሆነ ለትራምፕ በሚሰጠው ምላሽ ይወሰናል፡፡