ሩሲያ በፈጸመቻቸው መጠነ ሰፊ ጥቃቶች 25 ሰዎች መሞታቸውን ዩክሬን አስታወቀች
አሜሪካ ለኪየቭ የምታደርገውን ወታደራዊ ዕርዳታ ማቆሟን ተከትሎ የሩሲያ ጥቃቶች ተባብሰዋል

1 ሺህ 109ኛ ቀኑን ያስቆጠረውን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ለማስቆም ጥረቶች ቢደረጉም አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል
ሩሲያ በፈጸመቻቸው መጠነ ሰፊ ጥቃች 25 ሰዎች መሞታውን ዩክሬን ባለስልጣናት አስታወቁ።
ሩሲያ ባሳለፍነው አርብ ከባድ የተባለውን የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ነው የሰዎች ህይወት ያለፈው።
በጣም አስከፊው ጥቃት ከተባለው ውስጥ ባሳለፍነው አርብ እለት በዶኔትስክ ክልል ዶብሮፒሊያ ከተማ ውስጥ የተፈጸመው ነው ተብሏል።
በሁለት ባላስቲክ ሚሳዔሎች በ8 የመኖሪያ ህንጻ እና የገበያ ማዕከል ላይ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 11 ሰዎች መሞታቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥቃቱ በተፈጸመበት ስፍራ ላይ ከደረሱ በኋላ ሩሲያ ሌላ ጥቃት የፈጸመች ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ “ጥቃቱ ሆን ብሎ የተፈጸመ እና የሩሲያ ግብ አሁን እንዳልተቀየረ የሚያሳይ ነው” ብለዋል።
በዚያው በዶኔትስክ ክልል አርብ እና ቅዳሜ በተፈጸሙ ሌሎች ጥቃች 13 ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ሩሲያ በኦዴሳ ክልልም ጥቃት የፈጸመች ሲሆን፤ ይህ ጥቃት በሶስት ሳምንት ውስጥ ለ7ኛ ጊዜ በአካባቢው የኢነርጂ መሰረተ ልማት ኢላማ በማድረግ የተፈጸመ መሆኑን ባለስልጣነት አስታውቀል።
አሜሪካ ለዩክሬን ወታራዊ ድጋፍ እና የስለላ መረጃዎችን ማቅረብ ማቆሟ ተከትሎ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ጦርቱን በሰላም ስምምነት ለመቋጨት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ለማስቆም ቃል በገቡት ትራምፕ የሚመራው የአሜሪካ አስተዳደር ከሩሲያ ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል።