የታዋቂው ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ማርቲን ሉተር ኪንግ ልጅ ህይወቱ አለፈ
ደክስተር ስኮት የተሰኘው ይህ የማርቲን ሉተር ኪንግ ልጅ በ62 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል
የማርቲን ሉተር ኪንግ የመጨረሻ ልጅ የሆነው ደክስተር የጥቁር አሜሪካዊያን ታሪክን በመሰነድ ይታወቅ ነበር ተብሏል
የታዋቂው ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ማርቲን ሉተር ኪንግ ልጅ ህይወቱ አለፈ፡፡
ለጥቁር አሜሪካዊያን ህዝቦች ነጻነት በመታገል የሚታወቀው ማርቲን ሉተር ኪንግ በ1968 ላይ ነበር የተገደለው፡፡
ህልም አለኝ በሚለው ንግግሩ የሚታወቀው ይህ ጥቁር አሜሪካዊ አራት ልጆች ያሉት ሲሆን የመጨረሻ ልጁ የሆነው ደክስተር ስኮት በ62 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡
እንደ ኤፒ ዘገባ ደክስተር በፕሮስቴት ካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ሲሆን የአባቱን ህልሞች የማሳካት ፍላጎት እንደነበረውም ተጠቅሷል፡፡
የማርቲን ሉተር ኪንግ ህልምን ለማሳካት በሚል የተቋቋመው ኪንግ ማዕከል እንዳስታወቀው ደክስተር በአትላንታ ጆርጂያ ዩንቨርሲቲ ህግ ያጠና ሲሆን የአባቱን ህልም ለማሳካት፣ የአባቱን የአዕምሮ ውጤቶች እና ባለቤትነት ለማስከበር ጥረት ሲያደርግ እንደቆየም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ለዓመታት በካንሰር ህመም የቆየው ደክስተር አባቱ ማርቲን ሉተር ኪንግ ሲገደል የ7 ዓመት ህጻን ነበርም ተብሏል፡፡
ለቻይና ሚስጥር አሳልፎ ሰጥቷል የተባለው የአሜሪካ ባህር ኃይል አባል ታሰረ
የህንዱ ማህተመ ጋንዲ አድናቂ እንደሆነ የሚነገርለት ማርቲን ሉተር ኪንግ አራት ልጆች ያሉት ሲሆን ሁለቱ ሲሞቱ ሁለት ልጆቹ ደግሞ በህይወት እንዳሉ ተገልጿል፡፡
የማርቲን ሉተር ኪንግ የመጨረሻ ልጅ የሆነው ሟቹ ደክስተር ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት የሚታገሉ ሰዎችን መደገፍ፣ ለነጻነት ታግለው ህይወታቸው ያለፉ ጥቁር አሜሪካዊያን ተገቢውን ክብር እንዲያገኙ እና ታሪካቸውን መጪው ትውልድ እንዲረዳ የመሰነድ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷልም ተብሏል፡፡
ለአብነትም እንደ ሮዛ ፓርክ ያሉ ደማቅ የጥቁር ህዝቦች ትግል ያደረጉ ሰዎችን ታሪክ ለዓለም በማሳወቅ፣ ወደ ፊልምነት እንዲቀየር እና ሌሎችንም ድጋፎችን በማድረግም ዴክስተር ይታወቅ ነበር፡፡