ምባፔ ለሪያል ማድሪድ መጫወት የልጅነት ህልሜን ሙሉ ያደርግልኛል አለ
ምባፔ በሰባት አመት ቆይታው 256 ጎሎችን በማስቆጠር የፒኤስ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ክብረወሰን አስመዝግቧል
ምባፔ "ከልጅነቴ ጀምሮ መዳረሻዬ ሪያል ማድሪድ እንደሚሆን አውቅ ነበር" ሲል በበርናባው እስቴዲየም ለተሰባሰቡ ደጋፊዎቹ ተናግሯል
ምባፔ ለሪያል ማድሪድ መጫወት የልጅነት ህልሜን ሙሉ ያደርግልኛል አለ።
ፈረንሳያዊው አጥቂ ክሊያን ምባፔ እንድ ቀን ለሪያል ማድሪድ እንደሚጫውት ያምን እንደነበር እና ትምህርት ቤት ሳለም የስፔን ቋንቋን መማር መጀመሩን በትናንትናው እለት ተናግሯል።
ምባፔ "ከልጅነቴ ጀምሮ መዳረሻዬ ሪያል ማድሪድ እንደሚሆን አውቅ ነበር" ሲል በአብዛኛው የእሱ ስም ያለበትን ቲሸርት ለለበሱ በበርናባው እስቴዲየም ለተሰባሰቡ ደጋፊዎቹ ተናግሯል።
ከአቀባበል ስነ ስርአቱ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ምባፔ እንከንየለሽ የስፓኒሽ ቋንቋ መናገር መቻሉ ጋዜጠኞችን አስገርሟል። ምባፔ የስፓኒሽ ቋንቋ በትምህርት ቤት መማሩን እና በፓሪስ ሴንት ጀርሜን (ፒኤስጂ) የስፓኒሽ ቋንቋ ከሚናገሩት ሊዩስ ኢንሪኬ፣ማርሲዮ ፖቸቲኖ ከመሳሰሉት አሰልጣኞች ጋር በመነጋገር መለማመዱን ይናገራል። ምባፔ ይህን የሚያደርገው አንድ ቀን ህልሙ ወደ ሆነው ክለብ ቢገባ እንደማያስፈልገው ስለሚያውቅ ነው።
"ትምህርት ቤት ሳለሁ ምርጥ የምባል አልነበርኩም፤ ለሪያል ማድሪድ መጫወት ህልም ስለነበረኝ ቋንቋውን መናገር እንደሚጠቅመኝ አውቅ ነበር"ብሏል ምባፔ።
ሪያል ማድሪድ ባለፈው ሰኔ ወር ነበር ምባፔን ለአምስት አመት ማስፈረሙን ያስታወቀው። ክለቡ ምባፔን ለማስፈረም ለረጅም ጊዜ ጥረት አድርጎ የነበረ ቢሆንም በፈረንጆቹ ግንቦት 2022 አመት ከፒኤስጂ ጋር የነበረውን ኮንትራት በማራዘሙ ሳይሳካለት ቆይቷል።
በአቀባበል ስነስርአቱ ወቅት ምባፔ የ13 አመት ልጅ እያለ በፈረንጆቹ 2012 ሪያል ማድራድን ባስጎበኘው የሀገሩ ልጅ፣ የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ተጨዋች እና ስራ አስኪያጅ በሆነው ዚነዲን ዚዳን ነው ወደ መድረክ ያስተዋወቀው።
አጥቂው ምባፔ ሻሜፒዮንስ ሊግ እና ባላንዶር ባያሸንፍም፣ በሰባት አመት ቆይታው 256 ጎሎችን በማስቆጠር የፒኤስ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ክብረወሰን አስመዝግቧል።
ፈረንሳይ ከኦስትሪያ ጋር ባደገችው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ በአፍንጫው ላይ የመሰበር ጉዳት ካጋጠመው በኋላ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አድርጓል። እሱ እንደሚለው ከሆነ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል ወይም አያስፈልግም ወደሚል ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት የሪያል ማድሪድን የህክምና ቡድን እንደሚያማክር ተናግሯል።
የ25 አመቱ ምባፔ እንደ ቪንሺየስ ጁኒየር፣ ጁዴ ቤሊንግሀም የመሳሰሉ ኮከቦች ወደአሉበትና አምስት የሻፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎች በማንሳት በጣም ውጤታማ በሚባሉት አሰልጣን አንቸሎቲ ወደሚመራው ክለብ ተቀላቅሏል።