የ2023 የባላንድኦር እጩ ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ እነማን ተካተቱ?
ክርስቲኖ ሮናልዶ ከ2003 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የእጩዎች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል
ሜሲ ለ8ኛ ጊዜ በእጪነት ሲቀርብ፤ ከኤርሊንግ ሃላንድና ምባፔ ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቀዋል
ኮከብ የእግር ኳስ ተጨዋቾች የሚሸለሙበት ባላንድኦር የፈረንጆቹ 2023 የእጩ ተጫዋቾች ዝርዝር በትናንትናው እለት ይፋ ተደርጓል።
30 የእግር ኳስ ተጫዋቾች በእጩነት በተመረጡበት ዝርዝር ውስጥ የ5 ጊዜ የባላንድኦር አሸናፊው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ኖራልዶ ሳይካተት ቀርቷል።
ለሳዑዲ አረቢያው አል ናስር እየተጫወተ የሚገኘው ክርስቲያ ሮናልዶ ከባላንድኦር እጩ ተጫዋቾች ዝርዝር ውጪ ሲሆን ከፈረንጆቹ 2003 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም ታውቋል።
7 ጊዜ ባናድኦርን ያሸነፈው አርጀንቲናውዊ ኮከብ ሊዮኔል ሚሴ ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ ለማሸነፍ በእጩነት ዝርዝር ውስጥ ከሚገኙት ውስጥ ከፍተኛውን ግምት አግንቷል።
ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ሶስት ዋንጫዎችን ያነሳው እና በአንድ የውድድር ዓመት 50 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈው የማንቸስተር ሲቲው ኤርሊንግ ሃላንድም የ,በእጩነት የቀረበ ሲሆን፤ የአሸናፊነት ግምት ካገኙት ውስጥ ይገኛል።
ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 12 ተጫዋቾች ለባላንድኦር በእጩነት የቀረቡ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 7 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ካሸነፈው ማንቸስተር ሲቲ ነው የተመረጡት።
በዚህም ከማንቸስተር ሲቲ ኤርሊንግ ሃላንድ፣ ኬቪን ድብሮይነ፣ ጁሊያን አልቫሬዝ፣ ሩበን ዲያዝ፣ በርናንዶ ሲልቫ፣ ሮድሪ እና ጋቫርዲዮል ተመርጠዋል።
ከአርሰናል ቡካዮ ሳካ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ሲመረጡ፤ ከዚህ ቀደም በርካታ ተጫዋቾችን ሲያስመርጥ የነበረው ሊቨርፑል ዝንድሮ መሃመድ ሳላህን ብቻ አስመርጧል።
በተጨማሪም አንድሬይ ኦናና ከማንቸስተር ዩናትድ፣ ከአርጀንቲና ጋር ዋንጫ ያነሳው ኤምሊያኖ ማርቲኔዝ ደግሞ ከአስቶን ቪላ ተመርጠዋል።
በሰዑዲ ሊግ ከሚጫወቱት ውስጥ ለአል ኢትሃድ እየተጫወተ የሚገኘው የአምናው የባላንዶኦር አሸናፊ ፈረንሳያዊው ኮከብ ካሪም ቤንዝይማ እና ለአል ሂላል የሚጫወተው ያኒን ቦኑ በእጩነት ቀርበዋል።
ከፈረንሳይ ሊግ ዋን ለፒ.ኤስ.ጂ የሚጫወቱት ፈረንሳያዊው ኮከብ ኪሊያን ምባፔ እና ራንዳል ኩኖ ማዊ በአጩነበት ቀርበዋል።
ከጀርመኑ ባየር ሙኒክ ጀማል ሙሲያላ፣ ኪም ሚን ጃዬ እና ሃሪ ኬን በእጩነት መቅረባቸውም ተመላክቷል።
ከሪያል ማድሪድ ጁድ ቤሊንግሃም፣ ቬኒሽየስ ጁኒር እና ሉካ ሞድሪች የተመረጡ ሲሆን፤ ከባርሴሎና ደግሞ ኢክላይ ጎንዶጋን፣ ሮበርት ሉዋንዶውስኪ እና ሮድሪ፤ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ አንቶኒ ግሪዝማን ተመርጠዋል።