አርጀንቲና ከአውስትራሊያ፤ አሜሪካ ከኔዘርላንድስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው
የኳታሩ የ2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች በትናትናው መጠናቀቃቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የጀመራሉ።
በአነጋጋሪነቱ እና ባልተጠበቁ ውጤቶች የተጀበው የኳታር የዓለም ዋንጫ ወደ ጥሎ ማለፍ የተቀላቀሉ 16 ሀገራት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቀጣዩ ዝር ለማፍ የሚፋለሙ ይሆናል።
በዚህም መስረት በዛሬው እለት ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ምድብ በ በመሪነት ያጠናቀቀችው አርጀንቲና ከምድብ አራት 2ኛ ሆና ካጠናቀቀችው አውስትራሊያ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሚደረገው ጨዋታ ላይ አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና እየመራ 1000ኛ ፕሮፌሽናል ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።
በ22 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ለሀገሩ የተሰለፈው 35 ዓመቱ ሜሲ፤ የመጨረሻው ይሆናል በተባለው የኳታሩ የአለም ዋንጫም ቡድኑን እየመራ ለተናፋቂው ድል ይፋለማል።
በአርጀንቲና በኩል የአንሄል ዲ ማሪያ መሰለፍ በጉዳት ምክንያት አጠራጣሪ ሲሆን ከአውስትራሊያ በኩል የተሰማ የጉዳት ዜና የለም።
ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት በተገናኙባቸው 5 ጨዋታዎች አውስትራሊያ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለችም፣ አርጀንቲና አራቱን ስታሸንፍ በአንዱ አቻ ወጥተዋል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ምድብ አንድን በመሪነት ያጠናቀቀችው ኔዘርላንድስ ከምድብ ሁለት 2ኛ ከወጣችው አሜሪካ ጋር ይጫወታሉ።
በአሜሪካ በኩል በኢራኑ ጨዋታ ግብ ሲያስቆጥር ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ የወጣው ክርስቲያን ፑሊሲች ከጉዳቱ አገግሞ በዛሬው ጨዋታ ይሰለፋል ተብሏል።
ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት 5 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ኔዘርላንድስ 4ቱን ስታሸንፍ በአንዱ አሜሪካ ድል አድርጋለች።
ጨዋታው ከ45 ሺህ ተመልካቾች በላይ መያዝ በሚችለው በአህመድ ቢን አሊ ስቴዲየም ይደረጋል።