ሜታ ኩባንያ በዶናልድ ትራምፕ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ገጾች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ አነሳ
ሜታ ኩባንያ ከሶስት ዓመት በፊት ነበር ገጾቹን የዘጋው
ዶናልድ ትራምፕ አሁንም የሜታ ኩባንያ ህግን ካላከበረ እገዳው ሊቀጥል እንደሚችል አስጠንቅቋል
ሜታ ኩባንያ በዶናልድ ትራምፕ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ገጾች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ አነሳ።
የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ኩባንያ ባለቤት የሆነው ሜታ ኩባንያ በፈረንጆቹ 2021 ላይ የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገጾችን አግዶ ነበር።
ሜታ ኩባንያ በወቅቱ የዶናልድ ትራምፕን ገጽ ያገደው ፕሬዝዳንቱ ዜጎችን ለሁከት እንዲነሳሱ ቀስቅሰዋል በሚል ነው።
ኩባንያው አሁን ላይ ዶናልድ ትራምፕ የማህበራዊ ትስስር ገጾቹን መጠቀም እንዲችሉ መፍቀዱን አስታውቋል።
ይሁንና ዶናልድ ትራምፕ ከዓመታት በኋላ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ አሁንም ተገቢውን ህግ ካላከበሩ እገዳው እንደሚጣልባቸው አስጠንቅቋል።
የፊታችን ህዳር ወር ላይ በሚካሄደው ፕሮዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚወዳደሩ የሚጠበቁት ዶናልድ ትራምፕ እስካሁን የፌስቡክ ገጻቸውን መጠቀም አልጀመሩም።
እጩ ፕሬዝዳንቱ የቀድሞው ትዊተር ወይም የአሁኑ ኤክስ አካውንት በተመሳሳይ አካውንታቸው ተዘግቶባቸው እንደ ነበር ይታወሳል።
ኢለን መስክ ኩባንያውን ከገዛው ጀምሮ ግን በዶናልድ ትራምፕ ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ አንስቷል።
ይሁንና ዶናልድ ትራምፕ የኤክስ አካውንታቸውን አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅመዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ካሸነፉ የሜታ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግን እንደሚያስሩ ይታወሳል።