ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ ባጋጠመው ጉዳት ከኳታር የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነ
ሰኔጋላዊው ኮከብ ሀገሩ የዘንድሮውን አፍሪካ ዋንጫ እንድታነሳ ከፍተኛ ሚና እንነበረው ይታወሳል
የሳዲዮ ማኔ ጉዳት ለሰኔጋላዊያን አስደንጋጭ ዜና ነው ተብሏል
ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ ባጋጠመው የጅማት ጉዳት ከኳታር የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነ፡፡
ሳዲዮ ማኔ ጉዳቱ የደረሰበት ክለቡ ባየር ሙኒክ ከወርደር ብሬመን ጋር ባደረገውና 6-1 ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ነው፡፡ ደይሊ ሜይል L'Equipeን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ማኔ ሴኔጋል በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በምታደርጋቸው ጨዋታዎች ምንም አይነት ተሳትፎ አይኖረውም፡፡
የሰኔጋል ብሄራዊ ቡድን ኔዘርላንድስ፣ ኢኳዶር እና ኳታር በሚገኙበት ምድብ ላይ መሆኗ ይታወቃል፡፡
የሳዲዮ ማኔ ጉዳት የዓለም ዋንጫ በይፋ ሊጀመር ጥቂት ሳምንታት ሲቀረው የተከሰተ እንደመሆኑ ለብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴ እና መላ ሴናጋላዊያን አስደንጋጭ ዜና ነው ተብሏል፡፡
የማኔ አለመኖር በሴኔጋል ካምፕ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠሩ አይቀርምም ነው የተባለው፡፡
ማኔ እስካሁን በርካታ ዋነወጫዎችን ያነሳ እና 34 ጎሎችን በስሙ ያስቆጠረ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ሰኔጋላዊው ኮከብ የዘንድሮውን አፍሪካ ዋንጫ እንድታነሳ የነበርው ከፍተና ሚናም አይዘነጋም፡፡
በክረምቱ በ35 ሚሊየን ፓውንድ ከሊቨርፑል ባየርን የተቀላቀለው ማኔ በጀርመን ባሳለፈው የመጀመርያ የውድድር ዘመን ለክለቡ ድንቅ ብቃት ማሰየት የቻለ ተጫዋችም ነው፡፡
በሁሉም ውድድሮች 23 ጨዋታዎችን አድርጎ 11 ጎሎችን በማስቆጠር አራት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቷል።