በወንዶች የዘር ፍሬ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቂቀ ፕላስቲክ ምርቶች ተገኙ
ስንፈተ ወሲብ ባለባቸው ስድስት ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ በወንድ የዘር ፈሳሻቸው ላይ የፕላስቲክ ምርቶች ተገኝተዋል
ደቂቀ ፕላስቲኮቹ በምግብ እና መጠጥ መልኩ ወደ ሰውነታችን እንደሚገቡ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል
በወንዶች የዘር ፍሬ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቂቀ ፕላስቲክ ምርቶች ተገኙ፡፡
መቀመጫቸውን በአሜሪካ፣ ጀርመን እና ጣልያን ያደረጉ ተመራማሪዎች በጋራ ያደረጉትን የጥናት ውጤት ይፋ አድርገዋል፡፡
በሳይንስ ጆርናል ላይ ይፋ የተደረገው ይህ የጥናት ውጤት የፕላስቲክ ምርቶች ከስንፈተ ወሲብ እና መሀንነት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ይፋ ሆኗል፡፡
ስካይ ኒውስ ይህን ጥናት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የስንፈተ ወሲብ ችግሮች ባጋጠማቸው በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት በሁሉም የወንዴ የዘር ፈሳሽ ላይ ደቂቀ ፕላስቲክ ምርቶች ተገኝተዋል፡፡
የዘር ፈሳሽ ናሙናው በተወሰደላቸው ሰዎች ላይ ሰባት አይነት የፕላስቲክ ምርቶች የተገኘ ሲሆን የተገኙት ምርቶች በምግብ እና መጠጥ መልኩ ወደ ሰውነታችን የሚገቡ ናቸውም ተብሏል፡፡
የወንዶች የዘር ፍሬ መጠን ከግማሽ በመቶ በላይ መቀነሱ ተገለጸ
ይህ የጥናት ውጤት በታሪክ በሰው ልጅ የዘር ፍሬ ፈሳሽ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የደቂቀ ፕላስቲክ ወይም ማይክሮ ፕላስቲክ ምርቶች መገኘታቸውን አረጋግጧል፡፡
በጥናቱ መሰረት ደቂቀ ፕላስቲክ ምርቶች የወንድ የዘር ፈሳሽ እንዲቀንስ ፣ ለስንፈተ ወሲብ እና ለመሃንነት እንደሚዳርግ ይህ የጥናት አመላካች እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ጥናቱን የመሩት ዶክተር ራንጂት ራማሳሚ እንዳሉት ከዚህ በፊት በደማችን ውስጥ የፕላስቲክ ምርቶች ተገኝተው ስለ ነበር በወንዴ የዘር ፍሬ ላይ መገኘቱ ብዙ አልገረመንም ብለዋል፡፡
በደማቸው ውስጥ የደቂቀ ፕላስቲክ ምርቶች የሚገኙባቸው ሰዎች ለስትሮክ ፣ ልብ ህመም እና ያለ እድሜ ሞት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል፡፡