ከሰሞኑ ያጋጠመው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን (አይቲ) እክል ምን ያክል ጉዳት አስከተለ?
በርካታ አለማቀፍ ተቋማት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርአታቸው ላይ በተፈጠረ ችግር አገልግሎታቸው መታወኩ ይታወሳል
ማይክሮሶፍት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን (አይቲ) እክል ያስከተለውን ጉዳት ይፋ አድርጓል
ከሰሞኑ ያጋጠመው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን (አይቲ) እክል ዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ በኮምፒውተሮች እና የተለያዩ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎቹ ላይ ጉዳት ማስከተሉን ማይክሮሶፍት ኩባንያ አስታወቀ።
ባሳለፈነው ኃሙስ በርካታ አለማቀፍ ተቋማት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርአታቸው ላይ በተፈጠረ ችግር አገልግሎታቸው መታወኩ ይታወሳል።
ክራውድስትራይክ ከተሰኘ የሳይበር ደህንነት ኩባንያ ለደንበኞቹ በለቀቀው የሶፍትዌር ማዘመኛ ጋር ተያይዞ ባጋጠመ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን (አይቲ) እክል ነው የኩባያዎቹ አሰራ ለሰዓታት የታወከው።
ባሳለፈነው ኃሙስ ማለዳ ጀምሮ የተከሰተው ችግር ባንኮች፣ አየርመንገዶች እና የሚዲያ ተቋማትን ስራ ማስተጓጎሉም ተገልጿል።
ይህንን ተከትሎ ማይክሮሶፍት ኩባያ ዛሬ ባወጣው መረጃ ያጋጠመው የአይቲ እክል ከአገልግሎት ማስተጓጎል በተጨማሪ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱንም አስታውቋል።
በዚህም ከሶፍት ዌር ማዘመኛ ጋር ተያይዞ ባጋመተው የአይ መስተጓጎል 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ያህል ዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ኮምፒውተሮችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ቁሶች ላይ ጉዳት ማድረሱንአስታውቋል።
ማይክሮሶፍት በኮምፒውተሮቹ ላይ የደረሰው ጉዳት በታሪክ አስከፊው የሳይበር ጉዳት መሆኑን ነው ያስታወቀው።
ማይክሮሶፍት በሶፍት ዌር ማዘመኛው ለጉዳት ደርሶባቸው ከጥቅም ውጪ የሆኑ ኮምፒውተሮችን መልሶ ለአገልግሎት ለማብቃት ጥረት እያደረገ መሆኑን ነው የገለጸው።
ከሃሙሱ የአይቲ እክል ጀርባ ያለው ክራውድ ስትራይክ ማን ነው?
ዋና መቀመጫውን ኦስቲን ቴክሳስ ያደረገው ክራውድ ስትራይክ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ግዙፍ የዓለማችን ተቋማት ያለምንም ስጋት ስራቸውን እንዲሰሩ የሚያደርግ ሶፍትዌር ነው።
ከየትኛውም ተቋም ሆነ ሀገራት የሚቃጡ የበይነ መረብ ጥቃቶችን በማክሸፍ የሚታወቀው ክራውድ ስትራይክ ሶፍትዌር የበርካታ ሀገራት አየር መንገዶች፣ ባንኮች፣ ሚዲያዎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደንበኞች ናቸው።
በመላው ዓለም ከ29 ሺህ በላይ ተቋማት ደንበኞች ያሉት ይህ ኩባንያ የበይነ መረብ ጥቃቶችን መከላከል ዋነኛ ስራው ቢሆንም በባሳለፍነው ኃስ ራሱ ክራውድ ስትራይክ በለቀቀው ሶፍተዌር በርካታ ተቋማት ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል።
በፈረንጆቹ 2011 የተመሰረተው ክራውድ ስትራይክ ከ170 በላይ ሀገራት እየተጠቀሙት እንደሆነ ተገልጿል።
ጎግልን ጨምሮ አማዞን፣ ኢንቴል እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚፎካከረው ክራውድ ስትራይክ የደረሰበት ጥቃት ምንጩ እስካሁን ይፋ አልሆነም።