ልዩልዩ
በጣሊያኗ ሚላን መለስተኛ አውሮፕላን ከህንጻ ጋር ተጋጭቶ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ
በአደጋው የአውሮፕላኑ አብራሪ ሮማኒያዊው ቢሊየነርና የቤተሰቦቹ ህይወታቸው አልፏል
አውሮፕላኑ ከቢሮ ህንጻ ጋር የተጋጨ ሲሆን፤ ህንጻውና በአካባቢው የነበሩ ተሸከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል
በጣሊያን ሚላን ከተማ መለስተኛ የግል አውሮፕላን ከህንጻ ጋር ተጋጭቶ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
መለስተኛ የግል አውሮፕላኑ 8 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን፤ በአደጋውም በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የሁሉም ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቋል።
የአውሮፕላኑ አብራሪ ሮማኒያዊው ቢሊየነር የ68 ዓመቱ ዳን ፓትሬስኩ ሲሆን፤ ከባለቤቱ እና ከልጆቺ ጋር ህይወታቸው ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል።
አውሮፕላኑ ከቢሮ ህንጻ ጋር ነው የተጋጨው የተባለ ሲሆን፤ ህንጻው እና በአካባቢው የነበሩ ተሸከርካሪዎች በእሳት መጋየታቸውም ነው የተነገረው።
በአሁኑ ወቅትም አደጋው እንዴት ሊከሰት ቻለ የሚለውን ለመለየት ምርመራ መጀመሩ ታውቋል።
በስፍራው የነበሩ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ከሆነ ባለ አንድ ሞተሩ PC-12 የተባለው አውሮፕላን ከህንጻው ጋር ከመጋጨቱ በፊት በእሳት ተያይዞ እንደነበረ ተናግረዋል።