ግብጽ በ2015ቱ የአውሮፕላን አደጋ ለሞቱ ሩሲያውያን ቤተሰቦች ካሳ ልትከፍል ነው
ከዚያም ወዲህ ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ ሃገራት የበረራ አገልግሎት በቅርቡ መጀመሩ የሚታወስ ነው
በሽብርተኞች ጥቃት ያጋጠመ ነው በተባለለት አደጋ 217 ሩሲውያን ሞተዋል
ግብጽ በ2015ቱ የሲናይ በርሃ የአውሮፕላን አደጋ ሰለባ ለሆኑ ሩሲያውያን ቤተሰቦች ካሳ ልትከፍል ነው፡፡
ካይሮ በአደጋው የተጎዱ ቤተሰቦችን ለመካስ መስማማቷን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል፡፡
አደጋው በፈረንጆቹ 2015 ነበር ወርሃ ህዳር ላይ የደረሰው፡፡
ከሪዞርት ከተማዋ ሻርም አል ሼክ ተነስቶ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ይበር የነበረው ኤርባስ A-321 የመንገደኞች አውሮፕላን በማዕከላዊ ሲናይ በረሃማ ስፍራዎች ነበር አደጋ የገጠመው፡፡ አደጋው በሽብር ያጋጠመ ጥቃት እንደነበርም በወቅቱ ተገልጿል፡፡
በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ 217 ሰዎች ሙሉ በሙሉ በአደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡
የኤጄሬው አውሮፕላን አደጋ ሰለባዎች ሙትአመት ሲዘከር
ከዚያም ወዲህ በሁለቱ ሃገራት መካከል ይደረግ የነበረው በረራ ተቋርጦ ቆይቶ ባሳለፍነው ወር መባቻ ላይ ተጀምሯል፡፡
በሽብር ጥቃቱ ለሞቱት የሩሲያ ዜጎች ቤተሰቦች ካሳ ይከፈል በሚል ከግብፅ ወገን ጋር ስትወያይ መቆየቷንም ነው ቃል አቀባዩዋ የተናገሩት፡፡
ኢትዮጵያ ልታለማ ያቀደችውን የኒውክሌር ኃይል የተመለከቱ ሁለት ስምምነቶችን ከሩሲያ ጋር አደረገች
በካሳ የክፍያ ሂደት እና ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ እየተሰራ እንደሆነም ዛካሮቫ ገልጸዋል፡፡