የተመድ አነስተኛ አውሮፕላን በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ተከሰከሰ
አውሮፕላኑ 4 ሰዎችን ጭኖ የነበረ ሲሆን፤ ከተሳፋሪዎችበ1 ተጓዥ ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል
የተመድም ይሁን የዓለም የምግብ ፐሮግራም ስለአውሮፕላኑ እስካሁን ምንም አላሉም
የንበረትነቱ የተባሩት መንግስታት ድርጅት እንደሆነ የተነገረለት አነስተኛ አውሮፕላን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን መከስከሱ ተሰምቷል።
ET-AMl የሚል መጠሪያ ያለው መለስተኛ አውሮፕላንኑ ከድሬድዋ ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ እንደነበረ ታውቋለ።
አውሮፕላኑ ከድሬ ዳዋ ከተማ ከተነሳ በኋላ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮሞቦልቻ ወረዳ ቄሬንሳ ቀበሌ ጉራቻ ጋራ አሩ በተባለ ስፍራ መከስከሱን አል ዐይን ከወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አውሮፕላኑ ዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 አካባቢ መውደቁንም ነው ጽህፈት ቤቱ ያስታወቀው።
አውሮፕላኑ በውስጡ 4 ሰዎችን ጭኖ የነበረ ሲሆን፤ ከተሳፋሪዎች መካከል በአንደኛው ተጓዝ ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ወደ ድሬደዋ ለህክምና መላኩንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
አውሮፕላኑ በአካባው በነበረ በጭጋጋማ የአየ ር ንብረት ሳቢያ ሳይወድቅ እንዳቀረም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
አውሮፕላኑ ላይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና “United Nations Humanitarian Air service” ጽሁፍ ይነበብበታል።
ሆኖም ግን የተባሩት መንግሰታትም ይሁን የዓለም የምግብ ፐሮግራም ስለ ተከሰተከሰው አውሮፕላን እስካሁን ያሉት ነገር የለም።