በሩሲያ አሮጌ አውሮፕላን ተከስክሶ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ
አውሮፕላኑ በትናትናው እለት ባደረገው በረራ ከራዳር መሰወሩንም ታስ ዘግቧል፡፡
አውሮፕላኑ በሩሲያ ኤርፖርቶች ውስጥ የቴክኒክ ፍተሻዎችን ያለፈና እና 42 ዓመት ያገለገለ ነው ተብሏል
በሩሲያ ሩቅ ምስራቅ አንቶኖቭ አን -26 የሆነ አሮጌ የትራንስፖርት አውሮፕላን ተክስክሶ ተሳፍረው የነበሩት ስድስቱ ሰዎች መሞታቸውን የሩሲያ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ሚኒስቴር ሐሙስ አስታወቀ።
የሩሲያው ታስ የዜና ወኪል እንደዘገበው አውሮፕላኑ በሩሲያ ኤርፖርቶች ውስጥ የቴክኒክ ፍተሻዎችን ያለፈና እና 42 ዓመት ያገለገለ ነው፡፡አውሮፕላኑ በትናትናው እለት ባደረገው በረራ ከራዳር መሰወሩንም ታስ ዘግቧል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ሚኒስቴር በዛሬው እለት እንዳስታወሰው ለመድረስ አስቸጋሪ በሆነ የመሬት ክፍል ውስጥ ፍርስራሹን ማግኘቱንና የነፍስ አድን ቡድን ቦታውን ለመድረስ ከአምስት ሰዓታት በላይ መጓዙን ገልጿል፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በአደጋው ምክንያት በሕይወት የተረፉ የሉም ”ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሩሲያ የአቪዬሽን ደህንነት መመዘኛዎች መሻሻላቸው ይገለጻል፤ ነገር ግን በተለይ በሩቅ ምስራቅ የሀገሪቱ ክልሎች ውስጥ ያረጁ አውሮፕላኖችን የሚያካትቱ አደጋዎች የተለመዱ ናቸው፡፡ በሐምሌ ወር በአንቶኖቭ አን -26 በባለሁለት ሞተር ቱርቦፕፕ ተሳፍረው የነበሩት 28 ሰዎች በሙሉ በካምቻትካ እንዲሁም በሩቅ ምሥራቅ በደረሰ አደጋ ሞተዋል።