በኒጀር ደቡብ-ምዕራባዊ ግዛት ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 69 ሰዎችን ገደሉ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በኒጀር የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2021/11/05/243-125859-nigerrr_700x400.jpg)
የኒጀር መንግስት ለሁለት ቀን የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን አውጇል
በኒጀር ደቡብ ምእራብ ግዛት ታጣቂዎች በፈጸሙጽት ጥቃት 69 ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡
አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በኒጀር የተፈጸመውን ጥቃት ማውገዛቸውን ኤኤፍ ዘግቧል፡፡ሊቀመንበሩ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኙ ሲሆን ኒጀር ፈታኝ ሁኔታዎች በሚገጥሟት ህብረቱ ከኒጀር ጋር ይቆማል ሲሉም አጋርነታቸው ገልጸዋል፡፡
የተፈጸመው የሽብር ጥቃት የሳህል ቀጠና ህዝቦችም ሆነ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሽብርተኝነትን በከፍተኛ ሁኔታ መታገል እንደሚስፈልግ ያመላከተ ነውም ብሏል፡፡
በኒጀር ደቡብ-ምዕራባዊ ክፍል ትላበሪ ግዛት ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 69 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
ጥቃቱን ተከትሎ የኒጀር መንግስት ለሁለት ቀን የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ያወጀ ሲሆን፤ የጥቃቱ ፈጻሚዎች “ማንነት ያልታወቀ ቢሆንም” እስላማዊ ታጣቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡
አካባቢው ራሱን የእስላማዊ መንግስት ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር ግንኙነት ካለው የሚሊሺያ ቡድን ቁጥጥር ስር እንደቆየ ይነገራል።
አጥቂዎቹ ከራሳቸው ቡድን የሞቱባቸውን ሰዎች አስከሬን በመያዝ ወደ ማሊ ድንበር መሸሻቸውንም ነው የተገለጸው፡፡
ኒጀር ከማሊ. ከቡርኪና ፋሶ እና ናይጄሪያ ጋር በሚያዋስኗት ድንበሮቿ ላይ ከጅሃዳዊ ቡድኖች በርካታ ጥቃቶችን እያስተናገደች የምትገኝ ሀገር ናት።
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሀገሪቱ ደቡብ-ምዕራባዊ ክፍል ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከ500 በላይ ሰዎች ተገለዋል።