የዳሬይ-ዳዬ መንደር በመጋቢት ወር የ66 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ጥቃት ደርሶባት እንደነበረ ይታወቃል
በሞተር ብስክሌቶች የያዙ ታጣቂዎች ማሳቸውን ሲጠብቁ በነበሩ የኒጀሯ የዳሬይ-ዳዬ መንደር ነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት 13 ህጻናት ጨምሮ 37 ሰዎች ተገድሏል።
ጂሀዲስቶች ፈጽመውታል በተባለው ጥቃት ተከትሎም ኒጀር የሁለት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን ማወጇ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ባወጣው መግለጫ“ ሰንደቅ አላማዎች በመላ ሀገሪቱ ዝቅ ብለው የሚውለበለቡ ይሆናል ”ብለዋል፡፡በሕዝቡ መካከል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳሰበው መንግስት “ሽብርተኝነትን ለመወጋት እስከመጨረሻው ድል እንደሚታገል ”ያለውን ቁርጠኝነትም አረጋግጧል።
ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ እስላማዊ ዘመቻ በሚል ከምዕራባዊ ማሊ በኩል እየተስፋፋ የመጣው የጂሃዲስቶች ጥቃት ኒጀርም እያስቸገረ ይገኛል፡፡
በመጋቢት ወር የ66 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ጥቃት የደረሰባት ዳሬይ-ዳዬ ፣ የደም መፋሰሱን ከባድ በሆነበት በቲላ-ቤሪ ክልል ውስጥ የሚገኝ መንደር ነው፡፡መንደሩ የኒጀር ፣ የቡርኪና ፋሶ እና የማሊ ድንበሮች በሚዋሰኑበት፡ “ባለሶስት ድንበር” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በባንባንጎኡ ዞን ውስጥ ይገኛል።
አካባቢው ከአልቃይዳ እና ከእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጋር በተያያዙ በከፍተኛ ተንቀሳቃሽ ጂሃዲስቶች ጥቃቶች ውስጥ ቆይቷል።