ተመድ በኒጀር በወራት ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው ይችላል አለ
እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ውስጥ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች እስከ ግንቦት ድረስ ለከፍተኛ እጥረት ይጋለጣሉ
የተመድ ባለፈው የካቲት ወር ለኒጀር ሰብአዊ እርዳታ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ጠይቆ ነበር
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በሚቀጥሉት ወራት በኒጀር 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል አስታውቋል፡፡
ቢሮው እንዳስታወቀው ከእነዚህ ውስጥ 1.6 ሚሊዮን የሚሆኑት እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ውስጥ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ይጋለጣሉ ብሏል፤ ይህ በፈረንጆቹ ህዳር ወር ውስጥ ከተተነበየው በ30 በመቶ መጨመሩን አመልክቷል፡፡
ማስተባበሪያ ቢሮው እንደገለጸው ከፈረንጆቹ ሀምሌ እስከ ነሀሴ ባለው ጊዜ ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች ምግብ ያጥራቸዋል፡፡
የሀገሪቱ 30 በመቶ ህዝብ ወይም 686ሺ ህዝብ ያለበት የቲላበሪይ ምእራባዊ ጫፍ በምግብ እጥረት በከፍተኛ መጠን የሚጠቃ ይሆናል ብሏል ቢሮው፡፡ በግዛቱ እየጨመረ የመጣው ርሃብ፣ ቦታው ካለው የደህንነት ስጋት ጋር መከሰቱን የሰብአዊ እርዳታ ቢሮው አስታውቋል፡፡ ከዚህ አመት መጀመሪያ ጀምሮ ታጣቂዎቸ ባደረሱት ጥቃት 300 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
ቢሮው እንዳለውበሀገር ውስጥ የተፈናቀሉት ጨምሮ በቲሊባሪይ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልገዋል፡፡ ባለፈው በፈረንጆቹ የካቲት ወር ቢሮው 25 ሚሊዮን ህዝብ ካላት ኒጀር 2.1 ሚሊዮን የሚሆኑትን ለመርዳት 523 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጠይቆ ነበር፡፡