ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመጠቀቻት የወታራዊ ስለላ ሳተላይት ባህር ውስጥ ወደቀች
በትናንትናው እለት የመጠቀችው የመጀመሪያዋ የሰሜን ኮሪያ የወታደራዊ ስለላ ሳተላይ ተምዘግዝጋ ባህር ውስጥ መውደቁን ሮየሰተርስ ዘግቧል
ችግሩ የተከሰተው የሮኬቱ ሁለተኛ ደረጃ አገልግሎት በማቆሙ ክብደት ተሸካሚው ክፍል ወደ ባህር ውስጥ እንዳወድቅ አድርጎታል
በትናንትናው እለት የመጠቀችው የመጀመሪያዋ የሰሜን ኮሪያ የወታደራዊ ስለላ ሳተላይ ተምዘግዝጋ ባህር ውስጥ መውደቀበን ሮየሰተርስ ዘግቧል።
ችግሩ የተከሰተው የሮኬቱ ሁለተኛ ደረጃ ወይም ስቴጅ አገልግሎት በማቆሙ ክብደት ተሸካሚው ክፍል ወደ ባህር ውስጥ እንዳወድቅ አድርጎታል።
"ቾሊና ዋን" የተሰኘችው ይህች ሳተላይት የወደቀችው በሞተር እና በነዳጅ ሲስተም ላይ ባጋጠማት ችግር ነው ተብሏል።
የሰሜን ኮሪያ መንግስት ቴሌቪዥን ኬሲኤንኤ እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚቃኝ ሳተላይት ማምጠቋን ገልጾ ነበር።
ራዮንግ ቾል የሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ የጦር ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ጠፈርን ማእከል ያደረገ ቁጥጥር አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የምታደርገውን "ግዴለሽ" ወታደራዊ ልምምድ ለመከላከል አስፈላጊ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።
ኃላፊው ይህን ያሉት ከግንቦት 31 እስከ 11 ባሉት ቀናት ውስጥ ልታመጥቅ እንደምትችል ለጃፖን የድንበር ጠባቂ ካሳወቁ በኋላ ነው።
ራይ እንደገለጹት የጋራ ወታደራዊ ልመምዱ ሰሜን ኮሪያ ምላሽ ለመስጠት የጠላት መረጃ መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን ትገልጻለች።
የአሁኑን እና የወደፊቱን ስጋት እንደሚረዱ ራይ ገልጸዋል።
ጃፖን በበኩሏ በምንም መልኩ ሳተላይቷ ወደ ግዛቷ ግዛት የምትገባ ከሆነ መትታ እንደምትጥል አስጠንቅቃ ነበር።