ግለሰቡ በፈጸመው ወንጀል የሁለት ዓመት እስር ተላልፎበታል
ሚስቱን ንብረት ላለማውረስ ሲል መኖሪያ ቤቱን ያቃጠለው ሰው
ፍራንሲስ ማክጊርክ የ50 ዓመት እንግሊዛዊ ሲሆን ሀገሪቱ ካሏት ሚሊየነሮች መካከልም አንዱ ነው፡፡
ይህ የጎልፍ ስፖርተኛ ግለሰብ ከሚስቱ ጋር መፋታቱን ተከትሎ መኖሪያ ቤቱ በቀድሞ ሚስቱ ሊወሰድበት እንደሆነ ያስባል፡፡
ይህ ያንገበገበው ይህ ግለሰብ መኖሪያ ቤቱን ለማቃጠል ይወስናል፡፡ ይሁንና ይህንን ቤቱን በእሳት ካያያዘ በኋላ ለቀድሞ ሚስቱ በተደጋጋሚ ቤቱን በእሳት እያቃጠለው እንደሆነ መልዕክት ይልካል፡፡
ቦታው ባልተጠቀሰ ስፍራ የእራት ግብዣ ላይ ያለችው ሚስት ከቀድሞ ባሏ ለሚደርሳት መልዕክቶች ምላሽ ሳትሰጥ ትቀራለች፡፡
ከጎረቤታቸው ያለው መኖሪያ ቤት በእሳት መያያዙን ያስታዋሉ ሰዎች ጉዳዩን ለአደጋ ጊዜ ተቋም ማሳወቃቸውን ተከትሎ ወዲያውኑ ደርሰው እየተቃጠለ ያለውን ቤት መታደግ ችለዋል ተብሏል፡፡
ስትወሰልት የተያዘች ሚስት በባሏ እርዳታ የምትወደውን ሰው አገባች
አውቆ ይሁን ሳይስበው ቁልፉን ከበሩ መክፈቻ ላይ በውጨኛው በኩል ትቶት የነበረው ይህ ግለሰብ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ እርዳታ አብሮ ከመቃጠል እንደተረፈ ለየት ያሉ ክስተቶችን በመዘገብ የሚታወቀው ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ይህ ቤትም መጠነኛ ቃጠሎ ደርሶባትል የተባለ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ከመውደም ሊተርፍ ችሏል፡፡
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ይህ የጎልፍ ስፖርተኛም በፈጸመው ትፋት የሁለት ዓመት እስር የተላለፈበት ሲሆን ፍርድ ቤት ቅጣቱን ወደ ገደብ ቀይሮለታል ተብሏል፡፡
ይሁንና ግለሰቡ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ማንኛውንም አይነት ወንጀል ቢፈጽም እና ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ይህ የ2 ዓመት እስር ተፈጻሚ እንደሚሆንበት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡