ሞባይል ስልክ አብዝቶ መጠቀም ለጭንቅላት ካንሰር ያጋልጣል?
የዓለም ጤና ድርጅት የሞባይል ስክ እና ጭንቅላት ካንሰር ያላቸውን ዝምድና አሳውቋል
250 ሺህ በጎ ፈቃደኞች እና መራማሪዎች የተሳተፉበት ጥናት ውጤት ሞባይል ስልክ እና የጭንቅላት ካንሰርን ግንኙነት ይፋ አድርጓል
ሞባይል ስልክ አብዝቶ መጠቀም ለጭንቅላት ካንሰር ያጋልጣል?
የሰው ልጅ ተንቀሳቃሽ ስልክን ወይም ሞባይልን ከፈረንጆቹ ከ1990ዎቹ ጀምሮ መጠቀም መጠቀም ጀምሯል፡፡
ሞባይል ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን ህይወት ካቀለሉ ዘመን አመጣሽ ምርቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን ቀስ በቀስ የሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ምርት ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን ሞባይል ስልክ የራሱ ጥቅም እንዳለ ሆኖ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳሉትም አያጠያይቅም፡፡
በርካታ ተመራማሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ይፋ ያደረጓቸው የጥናት ውጤቶች በሞባይል ስልክ ላይ ያለው ጨረር ወይም ራዲየሽን የራሱ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት ሲሉ ቆይተዋል፡፡
ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆነው አድኖሲን ምንድን ነው?
ሰዎች በብዛት ሞባይል ስልክን ሲጠቀሙ ከስልኩ ላይ የሚለቀቁት ጨረሮች አዕምሮን በመጉዳት ለጭንቅላት ካንሰር ያጋልጣሉ የሚሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር ተብሏል፡፡
ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በቅንጅት የተሰራ አንድ ጥናት እንዳስታወቀው ሞባይል ስልክ የጭንቅላት ካንሰርን አያስከትም ተብሏል፡፡
ከ250 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት ህ ጥናት የጭንቅላት ካንሰር እና ሞባይል ስልክ ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸውም ዩሮ ኒውስ ጥናቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ለሰባት ዓመታት ተደርጓል የተባለው ይህ ጥናት ሞባይል ስልክ አብዝተው የሚጠቀሙ እና አልፎ አልፎ የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ምንም አይነት ልዩነት እንደሌለ ተገልጿል፡፡