ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በሕንድ የሀይማኖት መግለል የለም አሉ
የመብት ተሟጋቾች እና አሜሪካ የመብት ጥስቶች መፈጸማቸውን ሪፖርት አድርገው ነበር
የሙስሊሞችን እና የሌሎች አናሳዎችን መብት እንዲያከብሩ እና የመናገር ነጻነት እንዲያሻሸሉ ጥያቄ የቀረበላቸው ሞዲ ፣ መሻሻል የሚያስፈልገው የለም ብለዋል
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአሜሪካ ከፕሬዝደንት ባይደን ጋር በሰጡት መግለጫ በህንድ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ሀይማኖቶች ላይ ማግለል የለም ሲሉ የሚቀርብባቸውን ክስ አስተባብለዋል።
የመብት ተሟጋቾች እና አሜሪካ የመብት ጥስቶች መፈጸማቸውን ሪፖርት አድርገው ነበር።
ፕሬዝደንት ባይደን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በኋይትሀውስ በሰብአዊ መብት እና በዲሞክራሲያዊ እሴቶች ዙሪያ መነጋገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሙስሊሞችን እና የሌሎች አናሳዎችን መብት እንዲያከብሩ እና የመናገር ነጻነት እንዲያሻሸሉ ጥያቄ የቀረበላቸው ሞዲ ፣ መሻሻል የሚያስፈልገው የለም ብለዋል።
"ህገመንግስታችን እና መንግስታችን ዲሞክራሲን በተግባር አሳይቷል። በተግባር አሳይቷል ስል በዘር፣ በሀይማኖት እና በሀይማኖት ለማግለል ቦታ የለም" ብለዋል ሞዲ።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ሪፖርት በህንድ በሙስሊሞች፣ በሂንዱ ዳሊትስ፣ በክርስቲያኖች እና በሌሎች አናሳዎች አያያዝ ላይ ስጋት እንዳለው ገልጾ ነበር።
የመብት ተሟጋቾች እና የባይደን ዲሞክራቲክ ፖርቲ አባላት፣ ፕሬዝደንት ጉዳዩን በግልጽ ለሞዲ እንዲያነሱላቸው ሲያሳስቡ ቆይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲን ለመቃወም በርካቶች በኃይት ሀውስ አቅራቢያ ተሰባስበው ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።