ፖለቲካ
አሜሪካ፣ ቻይናን ለመገዳደር ከህንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ከፍ በማድረግ ጉዳይ ዙሪያ ተወያየች
ኦስቲን እና የህንድ አቻቸው ሁለቱ ሀገራት አስተማማኝ ትብብር ለማድረግ መስማማታቸውን የህንድ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል
የአሜሪካ እና የህንድ የአምስት አመት የመከላከያ ኢንዱስትሪ ትብብር ፍኖተ ካርታ የውጊያ እና የእንቅስቃሴ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያመርቱ ይረዳል ተብሏል
የአሜሪካ የመከላከያ ጸኃፊ ሊልዮድ ኦስቲን ከቁጥር አንድ የጦር መሳሪያ ገዥ ከሆነችው ህንድ ጋር ግንኙነታቸውን ከፍ ለማካደግ ተነጋግረዋል።
ባለስልጣናቱ እንደገለጹት ትብብራቸውን ከፍ ለማድረግ የፈለጉት ሁለቱም ሀገራት በቻይና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት እና ተንኳሽነት መቸገራቸውን በመግለጽ ነው።
ኦስቲን ህንድን የጎበኙት ህንድ ከረጅሞ ጊዜ የጦር መሳሪያ አቅራቢዋ ሩሲያ በመላቀቅ በሀገር ውስጦ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ማድረጓን ተከትሎ መሆኑ ተዘግቧል።
ኦስቲን እና የህንድ አቻቸው ሁለቱ ሀገራት አስተማማኝ ትብብር ለማድረግ መስማማታቸውን የህንድ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሀገራቱ በጋራ ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸውን የትብብር መስኮች መለየታቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የአሜሪካ እና የህንድ የአምስት አመት የመከላከያ ኢንዱስትሪ ትብብር ፍኖተ ካርታ የውጊያ እና የእንቅስቃሴ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያመርቱ ይረዳል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በስለላ፣ በቅኝት እንዲሁም በባህር ስለሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በትበብር ይሰራሉ።