ልዩልዩ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ጨምሮ ወደ ሶማሊያ የሚደረጉ ሌሎች በረራዎች በጊዜያዊነት ተቋረጡ
ንብረትነቱ የኬንያ የሆነ እቃ ጫኝ አውሮፕላን ዛሬ በአደን አዴ አየር ማረፊያ መከስከሱ ይታወሳል
በረራዎቹ የተቋረጡት በሞቃዲሾ ያጋጠመ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ በመኖሩ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ጨምሮ ወደ ሶማሊያ የሚደረጉ ሌሎች በረራዎች በጊዜያዊነት ተቋርጠዋል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ጨምሮ ወደ ሶማሊያ የሚደረጉ ሌሎች በረራዎች ከሞቃዲሾ ወደ ሌሎች አየር ማረፊያዎች እንዲዛወሩ እየተደረገ ነው፡፡
በረራዎቹ የሚዛወሩት ሞቃዲሾ የሚገኘው የአደን አዴ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በጊዜያዊነት በመዘጋቱ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ አለበለዚያም ወደ ጅቡቲ ለመብረር መገደዳቸው ነው ሶማሊ ጋርዲያን የአየር ማረፊያውን ባለስልጣናት ዋቢ አድርጎ የዘገበው፡፡
ዛሬ ንብረትነቱ የኬንያ ሲልቨርስቶን ኤር የሆነ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በአደን አዴ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተከስክሷል፡፡
በዚህም ምክንያት ነው አየር ማረፊያው ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት አቋርጦ የተዘጋው፡፡
ከኪስማዮ፣ጋሮዌ፣ሃርጌሳ እና ባይዶዋ ወደ ሞቃዲሾ ሊደረጉ የነበሩ በረራዎች መቋረጣቸውም ተዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁኔታውን በተመለከተ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በማህበራዊ ድረገጾቹም ሆነ በይፋዊ የድረገጽ አድራሻው የሰጠው ነገር የለም፡፡