ፖለቲካ
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ከኃላፊነት ተነሱ
ሶስት ወራት ስራ ላይ ያልተገኙት የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ከኃላፊነት ተነሱ
ውጭ ሀገር ከሶስት ወራት በላይ የቆዩት የባህርዳር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ከኃላፊነት ተነስተዋል
ውጭ ሀገር ከሶስት ወራት በላይ የቆዩት የባህርዳር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ከኃላፊነት ተነስተዋል
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር ማህሪ ታደሰ ለሶስት ወር ከ15 ቀናት ያህል ስራ ላይ ባለመገኘታቸው ምክንያት ከኃላፊነት መነሳታቸውን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለአል አይን አማርኛ በስልክ አረጋግጧል፡፡
ምክትል ከንቲባ ለአንድ ወር ያህል ፍቃድ የነበራቸው ቢሆንም ለሶስት ወራት በመቆየታቸው ከስራ እንዲነሱ መወሰኑን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
ዶክተር ማህሪ በውጭ ሀገር በተለይም በካናዳ ለረጅም አመት የኖሩ ሲሆን ለአማራ ክልል መንግስት የባህርዳርን ከተማ በከንቲባነት እንዲመሩ ከአንድ አመት በፊት ነበር የሾማቸው፡፡
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ከተፈቀደላቸው አንድ ወር በላይ ስለቆዩ ክልሉ ከስልጣን እንዲነሱ መወሰኑ ታውቋል፡፡
ዶክተር ማህሪ በፌስቡክ ገጻቸው በጹህፍ ስለሁኔታው ባይገልጹም “አመሰግናለሁ” የሚል መልእክት ያለው ምስል አስቀምጠዋል፡፡