በሰዓት 200 ኪ.ሜትር የሚበረው ድሮኑ 12 ሰዓታትን በተልዕኮ ውስጥ የመቆየት አቅም አለው
ኢራን ከታጠቀቻቸው ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ “ሞሃጀር-6” ተብሎ የሚጠራው እጅግ ዘመናዊ የውጊያ ድሮን ደቃሚው ነው።
ከምእራባውያን ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ ያለችው ኢራን “ሞሃጀር-6” የተባለ የውጊያ ዶሮኗን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገችው በፈረንጆቹ 2016 ሲሆን፤ በ2018 ደግሞ በስፋ በማምረት ጦሯን ማስታጠቅ እንደጀመረች ይነገራል።
“ሞሃጀር-6 (Mohajer-6) የሚል መጠሪያ የተሰጠው ድሮኑ እጅግ ዘመናዊና ገዳይ እንደሆነ የሚነገርለት ሲሆን፤ ከቤት አፈራሾች ድሮኖች መካከል አንዱ።
ክንፉ 10 ሜትር የሚረዝመው ድሮኑ ቆመቱ ከ5 ሜትር በላይ መሆኑ ይነገራል።
“ሞሃጀር-6 (Mohajer-6) ድሮን የቅኝት እና የውጊያ ተልእኮዎችን የማከናወን አቅምም ያለው ነው።
በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር የሚከንፈው “ሞሃጀር-6” የውጊያ ድሮን በተከታታይ 12 ሰዓታትን በተልዕኮ ውስጥ የመቆየት አስገራሚ ብቃት አለው።
ከመሬት እስከ 15 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ የመብረር አቅም ያለው ድሮኑ፤ አንድ ጊዜ በሞላው ነዳጅ ከ900 ኪሎ ሜትር የመብረር አቅም እንዳለውም ነው የተነገረው።
በውጊያ ወቅትም ጋይድድ ሚሳኤሎች የሚታጠቀው “ሞሃጀር-6” በሰከንዶች ውስጥ ኢላማዎቹን ማውደም ይችላል ተብሏል።
“ሞሃጀር-6” ቃይም የተሰኙ ጋይድድ ሚሳኤሎች የሚታጠቅ ሲሆን፤ ኢላማውን በከፍተኛ ብቃት በሰከንዶች ውስጥ ወደ ፍርስራሽነት የመቀየር አቅም አለው።