አዲሱ የጄት ጉልበት ያለው ድሮን ለአየር ለአየር ውጊያ የሚውል መሆኑም
የቱርክ የመከላከያ ተቋም ባይካር የጄት ጉልበት ያለው ወርቃማው አፕል የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኪዚሌማ አዲስ ድሮን ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል።
በብዛት ባይራክታር ድሮኖችን በማምረት የሚታወቀው ባይካር የመከላከያ ተቋም፤ አዲሱ የጄት ጉልበት ያለው ድሮን የመካከለኛ በረራውን ማድረግ መቻሉን አስታውቋል።
ባይካር የመከላከያ ተቋም እንዳስታወቀው ወርቃማው አፕል የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኪዚሌማ የውጊያ ድሮን ከኢስታንቡል 85 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኮርሉ ግዛት የአየር ኃይል ማዕከል የበረራ ሙከራ አድርጓል።
አዲሱ የጄት ጉልበት ያለው ድሮን ለአየር ለአየር ውጊያ የሚውል መሆኑም ተነግሯል።
ለመነሳት ጥቂት ስፍራ ብቻ የሚያስፈልገው ድሮኑ እስከ 1 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ክብደት ይዞ መነሳት የሚችል መሆኑም ተነግሯል።
በሰዓት ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ የሚከንፈው ድሮኑ እስክ 300 ሺህ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ግንኙነት መፍጠር ይችላል ነው የተባለው።