ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ወደ ቤተመንግስት ያመሩ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ይመክራሉ።
ፕሬዝዳንቱ እና ልኡካቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየምንም እንደሚጎበኙ ተገልጿል።
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፤ ከዚህ ቀደም የአቡዳቢ አልጋ ወራሽ በነበሩትበት ወቅት በ2018 በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
- ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አረብ ኤሚሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና መረጋጋት ላይ ዋነኛ አጋር ሆና ተቀጥላች አሉ
- ኦማን ለአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ የሀገሪቱን ከፍተኛ ኒሻን ሸለመች
የአረብ ኢምሬትስ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መስኮች ጠንካራ ትብብር መስርተዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል በከፍተኛ ባለስልጣናተ ደረጃ የተለያዩ ጉብኝቶች የተካሄዱ ሲሆን፤ በተለይም የፈረንጆቹ 2018 በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ በአዲስ አበባ እና አቡ ዳቢ የስራ ጉብኝቶች በተከታታይ መካሄድ የጀመረበት ነው።
የሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሁለቱ መንግስታት ህዝቦች ግንኙነት ቀጣይነት ያለው መሆኑ ማሳያ እና የአፍሪካ እና የአረብ ኢምሬትስ ግንኙነት አርአያ ሊሆን የሚችል መሆኑም ተነግሮለታል።