ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ፓሪስ ገቡ
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አቀባበል ተደርጎላቸዋል
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከፈረንሳይ አቻቸው ኢማኖኤል ማክሮን ጋር ይወያያሉ
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አልናህናያን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ፈረንሳይ ገቡ።
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት በፈረንሳይ ኤሊሴ ቤተ መንግስት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከፈረንሳይ አቻቸው ኢማኖኤል ማክሮን ጋር ይወያያሉ።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ እና በላቀ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ጨምሮ በትምህርት፣ ባህልና እና ሁለቱን ሀገሮች ከሚያገናኘው ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ጉዳይ ይመክራሉ፡፡
- ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ፈረንሳይን ለምን መረጡ?
- የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ስልጣን ከያዙ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ፈረንሳይ ገብተዋል
ሁለቱ ሀገራት በሁሉም አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እና የሁለቱን ሀገራት ፍላጎት እድገት እና የቀጣናውን ደህንነት እና መረጋጋት ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያሉ።
የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ የስራ ጉብኝታቸውን ባሳለፍነው ዓመት በፈረንሳይ ማድረግ መጀመራቸው ይታወሳል።
በጋራ ጥቅም ላይ እና በትብብር ላይ የተመሰረተው የፈረንሳይና ዩኤኢ የሁለትዮሽ ግንኙነት የተጀመረው በፈረንጆቹ 1971 ነበር።
አረብ ኢሚሬትስ ከፈረንሳይ ጋር ትብብር ስትመሰርት ሳይንሳዊ ነገሮችን ለማግኘት በማለስም ሲሆን በዚህም ሽብርተኝነትን፣ ጽንፈኝነትንና አጥፊነትን በመዋጋት ከፈረንሳይ ልምድ መቅሰሟ ይነገራል።
የፈረንሳይና የዩኤኢ ግንኙነት፤ ዩኤኢ ከተመሰረተችበት ከፈረንጆቹ 1971 ጀመሮ እምርታ አሳይቷል።