ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ከኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ ጋር ተወያይተዋል
ኦማን ለአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ የሀገሪቱን ከፍተኛ ኒሻን ማበርከትዋ ተገለጸ።
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ከትናንት ጀምሮ በኦማን ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው።
በጉብኝቱ ወቅትም የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ከኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተነግሯል።
በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥብቅ ግንኙነት ያወሱት መሪዎች፣ ወደፊት የአረብ ኢሚሬትስ እና የኦማን ህዝብን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ እና ኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ነው የተባለው።
የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ከኦማን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅ እጅም የሀገሪቱን ከፍተኛ የኒሻን ሽልማት ተቀብለዋል።
ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲጠናከር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው "አል ሰኢድ" የተባለውን የኦማን ከፍተኛ የኒሻን ሽልማት የተበረከተላቸው።
ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድም ለኦማን ሱልጣን ሃይትሃም ቢን ታሪቅ የአረብ ኢሚሬትስን ከፍተኛ የኒሻን ሽልማት አበርክተዋል።
በዚህም ኦማን ሱልጣን ሃይትሃም ቢን ታሪቅ “የዛይድ ሜዳል” የተባለ ከፍተኛ የአረብ ኢሚሬትስ የኒሻን ሽልማት ተቀብለዋል።