የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ልጆች ሊቨርፑልን ለመግዛት ጠየቁ
አላላ እና ጋማል የተሰኙት የግብፅ ፕሬዝዳንት ልጆች የእንግሊዙ ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብን ለመግዛት ጥያቄ አቅርበዋል
ሊቨርፑል እግር ክለብ ለሽያጭ መቅረቡ ይታወሳል
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ልጆች ሊቨርፑልን ለመግዛት ጠየቁ።
የእንግሊዙ ታላቅ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤቶች ከሶስት ቀናት በፊት የተወሰነውን የክለቡን ድርሻ መሸጥ እንደሚፈልጉ ማሳወቃቸው ይታወሳል።
ይሄንን ተከትሎም የቀድሞ የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ልጆች ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ የተወሰነ ድርሻ ለመግዛት በይፋ ጥያቄ አቅርበዋል ተብሏል።
የሆስኒ ሙባረክ ልጆች ሄርመስ የተሰኘ የፋይናንስ ግሩፕ ባለቤት ሲሆኑ የሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብን የተወሰነ ድርሻ ለመግዛት ማሰባቸው ተገልጿል።
ይህ የግብያውያኑ የፋይናንስ ኩባንያ ከካይሮ በተጨማሪ በብዙ ሀገራት ላይ እየሰራ እንደሆነም ተጠቅሷል።
ይሁንና ሄርመስ የተሰኘው ይህ የቀድሞ የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ልጆች ኩባንያ ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብን ጨምሮ በእግር ኳስ ቢዝነስ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አልገለጸም።
ፌንዌይ ስፖርት ግሩፕ የተሰኘው የሊቨርፑል ባለቤቶች በፈረንጆቹ 2010 ላይ ክለቡን ከቀድሞ ባለቤቶች የገዙት ሲሆን አሁን ደግሞ የተወሰነውን አክስዮን ለመሸጥ ማቀዳቸው ተገልጿል።
ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ የ2020 ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን እና የአውሮፓ ክለቦች ውድድር ዋንጫን ካነሳ በኋላ የክለቡ ዋጋ ጨምሯል።
በጀርመናዊው አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ የሚሰለጥኑት ሊቨርፑሎች በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ አጥጋቢ ውጤት እያስመዘገቡ አይደለም።