አረብ ኢሚሬትስ፣ ግብጽ እና ዮርዳኖስ “አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር ምእራፍ ነው” የተባለለት ስምምነት ተፈራረሙ
ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል የሚኖረውን የንግድ ልውውጥ መጠን የሚያሳድግ ነው ተብሏል
ግብርና፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ጨርቃጨርቅ፣ ማዕድን እና ፔትሮኬሚካል ሀገራቱ አብሮ ለመስራት የተስማሙባቸው የትብብር ዘርፎች ናቸው
አረብ ኢሚሬትስ፣ ግብጽ እና ዮርዳኖስ የተቀናጀ የኢንዱስትሪ አጋርነት ስምምነትን ለዘላቂ ኢኮኖሚ ልማት የሚል ይዘት ያለው ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራረሙ።
ስምምነቱ ሶስቱ ሀገራት የጋራ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ባላቸው አስፈላጊ እድሎችን ላይ ኢንቨስትመንቶችን በማፍሰስ በመካከላቸው የሚኖረው የኢኮኖሚ ትብብር ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያደርስ መሆኑም ነው የተገለተው፡፡
በሀገራቱ መካከል የተደረሰው ስምምነት “አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር ምእራፍ ነው”ም ተብሎለታል፡፡
በዛሬው እለት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዋና ከተማ አቡ ዳቢ ውስጥ የተደረሰው ስምምነት በአምስት የኢኮኖሚ ትብብር ማእቀፎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
‘ግብርና፣ምግብ እና ማዳበርያ’፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ጨርቃጨርቅ፣ ማዕድን እና ፔትሮኬሚካል ሶስቱም ሀገራት ያለሙትን የኢኮኖሚ ልማት እውን ለመድረግ በጋራ ከሚሰሩባቸው ዋና ዋና የትብብር ዘርፎች ናቸውም ተብለዋል፡፡
አጋርነቱ በሶስቱ ሀገራት ያለውን ለኢንዱስትሪ ምቹ የሆነ ሁኔትን በመጠቀምና የትብብር ማእቀፎች በማስፋት (ቀጣይነት ያለው እድገት፣ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎችን በማጎልበት፣ እሴት የተጨመረባቸው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎችን በማስተዋወቅ) እንዲሁም ስትራቴጂካዊ ግቦችን ከግብ በማድርስ ይበልጥ እንደሚጠናከር ይጠበቃል፡፡
ይህም በሀገራቱ መካከል የሚኖረው የንግድ ልውውጥ መጠን እንዲያድግና የኢኮኖሚ ውህድት እንዲፈጠር የሚያስችል መሆኑ ተገልጸዋል፡፡