ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ ከህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያዩ
የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ አረብ ኢምሬትስን እየጎበኙ ነው
ሁለቱ ሀገራት ንግዳቸውን ለማሳደግ በየራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት ተስማምተዋል
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ከህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያዩ።
የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢንዛይድ አልናህያን ለጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
አረብ ኢምሬትስን ለአምስተኛ ጊዜ እየጎበኙ ያሉት የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሁለትዮሽ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል።
የሁለቱ ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት መጠን ከ84 ቢሊዮን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን አረብ ኢምሬት ዘይት ወደ ህንድ በመላክ ከቀዳሚዎች ቱርታ የተሰለፈች ሀገር ናት።
ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ የተስማሙ ሲሆን ግብይታቸውን በሩጲ እና ድርሀም ለማድረግም ተስማምተዋል ተብሏል።