ፖለቲካ
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት 'የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽን' ሲከፈት ታድመዋል
በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነው ተመርቆ የተከፈተው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2023/8/20/243-202558-img-20230819-wa0002-1-_700x400.jpg)
የውሃ እና ኢነርጂ ኤግዚብሽን የተካሄደበት የሳይንስ ሙዚየም ሁለት ህጻዎች ያሉት ሲሆን ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ከትናንት በስትያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ 'የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽን' ሲከፈት ታድመው ነበር።
በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነው ተመርቆ የተከፈተው።
የኢምሬት ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነሀያን በኤግዚቢሽኑ ላይ የተለያዩ ሁነቶች ተመልክተዋል፤ በውሃና ኢነርጂ መስክ ከተሰማሩ ተሳታፊዎች ጋር ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
ለተሳታፊዎች ያሰቡት እንዲሳካላቸው ምኞታቸውን የገለጹት ኘሬዝደንቱ የሳይንስ ሙዚየሙን በርካታ ክፍሎች ጎብኝተዋል።ፕሬዘደንቱ የሙዚየሙን አካባቢን ለመንከባከብ በሚያችል መልኩ መሰራቱን አድንቀዋል።
የውሃ እና ኢነርጂ ኤግዚብሽን የተካሄደበት የሳይንስ ሙዚየም ሁለት ህጻዎች ያሉት ሲሆን ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር።