ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቤት አልባ ናቸው ተባለ
እነዚህ ዜጎች አስቸኳይ መሰረታዊ ድጋፎች ያስፈልጋቸዋልም ተብሏል
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ 12 ሚሊዮን ዜጎች የሚጠጣ ውሃ እጥረት አለባቸውም ተብሏል
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቤት አልባ መሆናቸውን ተመድ ገለጸ፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ሀገራት የተወሰኑ አካባቢዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል፡፡
የተመድ ቃል አቀባይ ፋርሃን ሀቅ እንዳሉት በአፍሪካ ቀንድ ከ1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቤት አልባ ሆነዋል፡፡
በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ፣ኬንያ እና ሶማሊያ 12 ሚሊዮን ዜጎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር ገጥሟቸዋልም ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡
በምስራቅ አፍሪካ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በኑሮ ውድነትና ግጭት ምክንያቶች እየሞተ ነው ተባለ
በድርቁ በተለይም ሴቶች እና ህጻናት የበለጠ ጉዳት እያስተናገዱ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ለተጎጂዎች በቶሎ ድጋፍ ማድረግ ካልተቻለ በታሪክ አስከፊውን ጉዳት ያስተናግዳሉም ብለዋል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ በአጠቃላይ 18 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች አስከፊ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ድርጅቱ የተናገረ ሲሆን 200 ሺህ ሶማሊያዊያን መራባቸው ተገልጿል፡፡
ከዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በተገኘ ድጋፍ እስካሁን 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎችን መርዳት የተቻለ ሲሆን ለተቀሩት ዜጎች በጀት ባለመገኘቱ ምክንያት ለረሃብ የሚጋለጡ ዜጎች መኖራቸውን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡