ተመድ በየመን የታሰሩ 6 ሺ 750 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ሊመልስ ነው
የመን እ.ኤ.አ በ2014 የሁቲ አማጽያን ሰነዓን ከተቆጣጠሩ ወዲህ በእርስ በርስ ግጭት እየተናወጠች የምትገኝ ሀገር መሆኗ ይታወቃል
ባለፈው አመት 27 ሺ 700 የሚጠጉ ስደተኞች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን አድካሚ ጉዞ ማድረጋቸው ይነገራል
የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ በመጪዎቹ ወራት ቢያንስ 6 ሺ 750 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በጦርነት በመታመስ ላይ ካለቸው የመን ለማስመለስ ማቀዱን አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ስደተኞቹን ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጠይቋል።
ባለፉት ወራት በሶስት በረራዎች ከ600 በላይ ስደተኞችንና ቤተሰብ የሌላቸው 60 ህጻናትን ወደ ኢትዮጵያ ማዘዋወሩን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቋል።
በደቡብ የመን የወደብ ከተማ ኤደን እና በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መካከል ተጨማሪ በረራዎች ለማድረግ እቅድ እንዳለም ገልጿል ድርጅቱ፡፡
500 ዓመታትን ያስቆጠረው እና በዓለት ላይ የተመሰረተው የየመን መንደር
በየመን የአይ.ኦ.ኤም ዋና ኃላፊ ክሪስታ ሮተንስታይነር “በየመን የሚያልፉ ወይም የሚቆዩ ስደተኞች በሀገሪቱ ባለው ቀውስ መባባስ የሰብአዊ ሁኔታ በጣም ከተጎዱት መካከል ናቸው” ብለዋል።
የየመን የእርስ በርስ ግጭት ስራ ለማግኘት በሚል ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚጓዙ ስደተኞችን አላስቀረም ሲልም ነው ድርጅቱ ያስታወቀው፡፡
ባለፈው አመት 27 ሺ 700 የሚጠጉ ስደተኞች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን አድካሚ ጉዞ ማድረጋቸውን የአይ.ኦ.ኤም መረጃ ያመላክታል።
የመን እ.ኤ.አ በ2014 በኢራን የሚደገፉ የሁቲ አማጽያን ዋና ከተማዋን ሰነዓን እና አብዛኛው ሰሜናዊ ክፍሏን ከተቆጣጠሩ ወዲህ፤ በእርስ በርስ ግጭት እየተናወጠች ትገኛለች፡፡
አማጽያኑ ወታደራዊ ይዞታዎቻቸውን በማስፋት፤ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የሃገሪቱ መንግስት ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል ከዚያም በሳዑዲ አረቢያ በግዞት እንዲሰደድ ማስገደዳቸው ይታወሳል።