ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሱዳን ክፍያውን እንደፈጸች ሽብርን ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ስሟ ይሰረዛል ብለዋል
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሱዳን ክፍያውን እንደፈጸች ሽብርን ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ስሟ ይሰረዛል ብለዋል
የሱዳን አዲሱ መንግስት ለአሜሪካውያን የሽብር ሰለባዎችና ቤተሰቦቻቸው የ335 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል መስማማቱን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሱዳን ክፍያውን እንደፈጸች ሽብር ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ትሰረዛለች ብለዋል፡፡”በመጨረሻም የአሜሪካ ህዝብ ፍትህ አገኘ፤ ለሱዳንም ትልቅ እርምዳ ወደፊት ነው” ሲሉ ስምምነቱን አድንቀዋል፡፡
ከሁለት 10 አመታት በፊት በታንዛኒያና በኬንያ በሚኘኑት የአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ በደረሰው ጥቃት በኢምባሲዎቹ ሲሰሩ የነበሩ አሜሪካውያን መሞታቸውን ተከትሎ አሜሪካ ለጥቃቱ ሱዳንን ስትወንጅል ቆይታ ነበር፡፡
ሱዳን አሸባሪዎችን በመደገፍ ነው ይህ ድርጊት የተፈጠረው ስትል አሜሪካ ብትከስም ሱዳን አትቀበለውም ነበር፡፡
ሱዳንን 30 አመታት ለሚጠጋ ጊዜ የመሩት አልበሽር በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2019 ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የመጣው አስተዳደር ማእቀቡ እንዲነሳ ፋላጎት ነበረው፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዎ ወደ አፍሪካ ባደረጉት ጉዞ ሱዳንንም መጎብኘት ችለው ነበር፡፡