በ2019 የጀመረው የሱዳን የሽግግር ጊዜ በ2024 መጀመሪያ ላይ በምርጫ ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር
የሱዳን ጦር ለሲቪል አገዛዝ መመስረት ቁርጠኛ ነኝ አለ፡፡
የሱዳን ጦር ሀገሪቱን ወደ ሲቪል አገዛዝ ለሚያመራው የፖለቲካ ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግሯል።
ሰራዊቱ በሰጠው መግለጫ "ስልጣን ለመጨበጥ የትኛውም አካል፣ ፓርቲ ወይም ቡድን መወጣጫ አልሆንም" ብሏል።
"የሱዳን ጦር ኃይል የሲቪል መንግስት መመስረትን ወደሚያመራው የፖለቲካ ሂደት ቁርጠኛ ነው" ሲል ገልጿል።
የሱዳን ጦርነት ለጎረቤት ሀገራት ያለው ዳፋ ምንድን ነው?
የሱዳን ግጭት ከተቀሰቀበት ከሚያዝያ 15 ጀምሮ ቢያንስ 512 ሰዎች መገደላቸውንና ከአራት ሽህ በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ገልጿል።
ጦሩ ቅዳሜ እለት የሱዳንን ስልጣን ለመያዝ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በኩል ተደረገ ያለውን ሙከራ ማክሸፉን ተናግሯል።
በቅርብ ወራት ውስጥ በወታደራዊ ደህንነት ማሻሻያ ዙሪያ በጦሩ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል አለመግባባት መፈጠሩን አኖዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ሱዳን ከፈረንጆቹ ጥቅምት 2021 ጀምሮ መንግስት አልባ ሆና ቆይታለች ያለው ዘገባው፤ ወታደራዊው ኃይል የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን የሽግግር መንግስት ካሰናበተና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኋላ የፖለቲካ ኃይሎች እርምጃ “መፈንቅለ መንግስት” ሲል ፈርጀውታል።
ነሐሴ 2019 የጀመረው የሱዳን የሽግግር ጊዜ እ.አ.አ በ2024 መጀመሪያ ላይ በምርጫ ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር።