ጦርነት የተቀሰቀሰባቸው ሱዳን ካርቱምና አካባቢው አዳር ምን ይመስላል?
በጦርነቱ ከ56 በላይ ንጹሀን ሲገደሉ ከ590 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል
የሱዳን ወታደሮች ለሁለት ተከፍለው እርስ በርስ ሲዋጉ ዛሬ ሁለተኛ ቀናቸው ላይ ይገኛሉ
ጦርነት የተቀሰቀሰባቸው ሱዳን ካርቱም እና አካባቢው አዳር እንዴት ነበር?
የሱዳን ብሔራዊ ጦር የዳርፉር የጎሳ ግጭትን ለማስቆም ከ10 ዓመት በፊት የተቋቋመው የፈጠኖ ደራሽ አጋዥ ኃይል (አር.ኤስ.ኤፍ) ኃይሎች መካከል ጦርነት ከተጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል።
በሱዳን ስልጣን በበላይነት ለመያዝ እየተደረገ ባለው በዚህ ጦርነት በዋናነት በሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል አልቡርሀን እና በአርኤስኤፍ አዛዥ ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ዋነኛ ተፈላላጊዎች ሆነዋል።
ጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ ኤርፖርቶች እና ወታደራዊ ማዘዣዎችን ተቆጣጥሬያለሁ ቢሉም መከላከያ ሰራዊት ግን ውድቅ አድርጓል።
የሱዳን ዶክተሮች ኮሚቴ በበኩሉ በጦርነቱ እስካሁን ከ56 በላይ ንጹሀን መሞታቸው ሲገለጽ ከ560 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጿል።
አዳሩን ትንሽ ጋፕ ብሎ የነበረው ጦርነት ከንጋት ጀምሮ ዳግም እየተካሄደ ሲሆን ትናንት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ሳይቀር ውጊያው እየተስፋፋ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የሀገሪቱ መከላከያ እንዳሳወቀው የአርኤስኤፍ ሀይሎች ዋና ዋና ካምፖች ላይ የአየር ላይ ድብደባ ማካሄዱን አስታውቋል።
ተጨማሪም የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በጋዳሪፍ ክልል የሚገኘውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና ማዘዣን መቆጣጠሩን እታውቋል።
አሁንም ታጣቂዎች በሀገሪቱ ከተሞች ውስጥ መኖር አለመኖራቸውን የአየር ላይ ቅኝት እያደረገ መሆኑን የገለጸው የሱዳን መከላከያ ዜጎች ከቤት እንዳይወጡም አሳስቧል።
ይህ በዚህ እንዳለም ጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ ከሩሲያው ዋግነር ቅጥረኛ ወታደራዊ ቡድን ድጋፍ እየተደረገላቸው ስለመሆኑ እየተዘገበም ይገኛል።