ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በየቀኑ ከአንድ ሽህ በላይ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው አለ
ስደተኞቹ ከ50 በላይ የውጭ ሀገራት ዜጎች በተጨማሪ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብሏል
የሱዳን ግጭትን ለመሸሽ ከ12 ሽህ በላይ ሰዎች በኢትዮጵያ ድንበር መውጣታቸው ተነግሯል
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንዳስታወቀው በየቀኑ ከአንድ ሽህ በላይ ሰዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው።
ድርጅቱ በድረ-ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ በሽህዎች የሚቆጠሩ ሱዳናዊያንና ኢትዮጵያውያን እየተሰደዱ ነው።
መግለጫው ከቱርክ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ እና ከ50 በላይ ሀገራት ዜጎች በተጨማሪ አብዛኞቹ ስደተኞች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ጠቁሟል።
ድርጅቱ የሱዳን ግጭት ከተቀሰቀሰ ከሦስት ሳምትታት በኋላ በኢትዮጵያ ድንበር ከ12 ሽህ በላይ ሰዎች ወጥተዋል ብሏል።
"ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ከመመለሳቸው በፊት መጠለያን ጨምሮ አስፈላጊውን እርዳታ አደርጋለሁ" ሲል መግለጫው አክሏል።
በሱዳን በሚገኙ ግዛቶች በጦር ኃይሉ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ከፍተኛ ግጭት እየተካሄደ ሲሆን፤ ሁለቱ ወገኖች ለቀውሱ መከሰት ጣት እየተቀሳሰሩ ነው።