በተደጋጋሚ የሚጣሰው የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች 'ተኩስ አቁም ስምምነት' ጉዳይ
በሱዳን በአንድ ወቅት አጋር በነበሩት ሁለት ጀነራሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት ከሁለት ሳምንታት በላይ ሆኖታል
ሁለቱ ኃይሎች ለመጀመሪያ ጊዜ በረመዳን ወቅት ለ72 ሰአታት ተኩስ ለማቆም ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ተኩሱ ተከፍቶ ነበር
የሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋል ወይም ሄሜቲ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተኩስ ለማቆም በተለያየ ጊዜ ቢስማሙም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም።
በአንድ ወቅት አጋር በነበሩት ሁለት ጀነራሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት ከሁለት ሳምንታት በላይ ሆኖታል።
ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን ቢገልጹም ተፋላሚዎቹ በተግባር ለስምምነቱ ተገዥ መሆን አልቻሉም።
ሁለቱ ኃይሎች ለመጀመሪያ ጊዜ በረመዳን ወቅት ለ72 ሰአታት ተኩስ ለማቆም ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ተኩሱ በድጋሚ ተከፍቶ ነበር።
ሱዳናውያን በዓሉን በወጉ ማሳለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
እነዚህ ኃይሎች ከሳምንት በፊት በአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ጫና አማካኝነት ተኩስ ለማቆም ለ2ኛ ጊዜ መስማማታቸውን ገልጸው ነበር።
ይህ ስምምነት ከመጀመሪያው ተኩስ አቁም ስምምነት አንጻር ሲታይ በከፊል ተግባራዊ ሆኖ እንደነበር ተመድ ገልጾ ነበር።
በዚህ ወቅት የተለያዩ ሀገራት በድንገት በተቀሰቀሰው ጦርነት ችግር ውስጥ ገብተው የነበሩ ዲፕሎማቶቻቸውን እና ዜጎቻቸውን ማውጣት ችለው ነበር።
ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት ጊዜ ካለቀ በኋላ ተፋላሚ ኃይሎቹ ስምምነቱን ለማራወም ፍላጎታቸውን ገልጸው ስምምነቱ መራዘሙ በዛሬ እለት ተገልጿል።
ይህ የኩስ አቁም ስምምነት ለ 7 ቀናት መራዘሙን እና ስምምነት እንዲደረስ ያደራደሩት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር መሆናቸውን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ነገርግን አሁንም ስምምነቱ ተጥሶ በሱዳን የአየር ድብደባ እየተፈጸመ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሁለቱ ተፋላሚዎች ለደረሷቸው ተኩስ አቁም ስምምነቶት ተገዥ የማየሰሆኑት እንዳቸው ሌላኛቸውን እንደሚያሸንፉ ማመናቸው ነው ተብሏል።
ሱዳን ከሶስት አስርት አመታት በላይ ያስተዳደሩት አል በሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ከወረዱ ወዲህ ሀገሪቱ የማያባራ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች።