ሞሮኮ ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል የዓለም ዋንጫን በማዘጋጀት ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለች
ሞሮኮ በካዛብላንካ አቅራቢያ በምትገኘው ቤንስሊማኔ ትልቅ ስቴዲየም ለመገንባት ማቀዷን አስታውቃለች።
የ2030 የዓለም ዋንጫ የጋራ አዘጋጅ የሆነችው ሞሮኮ ከአዲስ ግንባታ በተጨማሪም ሌሎች ስድስት ስቴዲየሞችን ለማደስ ማቀዷን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
አዲሱ ስቴዲየም በ2028 ለማጠናቀቅ 500 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፤ በመንግስት እና ሲዲጂ በተባለ መንግስታዊ ተቋም መካከል ስምምነት ተፈርሟል።
የሚታደሱት ስታዲየሞች በ2025 የአፍሪካ ዋንጫን እና በ2030 ደግሞ የዓለም ዋንጫን ያስተናግዳሉ ተብሏል።
ስድስቱ ስታዲየሞች በአጋድር፣ ካዛብላንካ ፌዝ፣ ማራካሽ፣ ራባት እና ታንጊር ከተሞች እንደሚገኙ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ገልጿል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ፊፋ የ2030 የዓለም ዋንጫን ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል እንዲያስተናግዱ መርጧል።
በተጨማሪም ኡራጓይ፣ አርጀንቲና እና ፓራጓይ የውድድሩን 100ኛ ዓመት ለማክበር ሦስት ጨዋታዎችን እንደሚያዘጋጁ ፊፋ ተናግሯል።
ሞሮኮ ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል የዓለም ዋንጫን በማዘጋጀት ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለች።