ከልጁ እና ወላጆቹ አንዳቸውን የመምረጥ ግዳታ ውስጥ የገባው ሞሮኳዊ
በሞሮኮ በተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ከ2 ሺህ 500 አልፏል
አደጋው ሀገሪቱ በ60 ዓመት ውስጥ አጋጥሟት አይውቅም ተብሏል
ከልጁ እና ወላጆቹ አንዳቸውን የመምረጥ ግዳታ ውስጥ የገባው ሞሮኳዊ
በሞሮኮ ከትናት በስቲያ በተፈጠረ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር በየጊዜው እያሻቀበ ይገኛል፡፡
በፍየል እርባታ የሚተዳደረው ታይብ ኢግንባዝ ከሁለት ልጆቹ፣ ሚስቱ እና ወላጆቹ ጋር በአንድ ግቢ ውስጥ ነበር የሚኖረው፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ በተከሰተው አደጋ ተጎጂ ከሆኑ የሞሮኮ ዜጎች መካከል አንዱ ሲሆን አደጋው ከተከሰተ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ራሱን ከቤት ፍርስራሾች መካከል ያገኘዋል፡፡
ቀሪ ቤተሰቦቹን ሲፈልግ የ11 ዓመት ልጁ እና ወላጆቹ ጎን ለጎን ቤት ተደርምሶባቸው ሲያጣጥሩ ያገኛቸዋል፡፡
በዚህ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ በሆነበት ቅጽበት ቀድሞ ማንን ማዳን እንዳለበት ግራ ይጋባል፡፡ የግድ መወሰን ነበረበት እና ልጁን ከፍርስራሹ ውስጥ እንዲወጣ ረድቶት እና ተሳክቶለት ወዲያውኑ ወደ ወላጆቹ ሲመለስ ህይወታቸው አልፎ እንዳገኛቸው ለቢቢሲ በእንባ ታጅቦ ተናግሯል፡፡
በሞሮኮ የአየር ንብረት ለውጥ "አፈታሪክ" ነው የሚሉ አሉባልታዎች እየተሰራጩ ነው
እናት እና አባቴ ህይወታቸው ሲያልፍ በአይኔ ነው ያየሁት የሚለው ታይብ አደጋው እጅግ ሰቅጣጭ እና ልብ ሰባሪ እንደነበር ገልጿል፡፡
ወላጆቼን፣ ጥሬ ገንዘቦቼን እና ፍየሎቼን በአደጋው አጥቻለሁ የሚለው የ50 ዓመቲ ታይብ ህይወትን እንደ አዲስ ሀ ብዬ ለመጀመር ተገድጃለሁ ብሏል፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ፍለጋቸውን አሁንም የቀጠሉ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
እስከዛሬ ድረስም በአደጋው ህይወታቸው ያለፉ ዙጎች ቁጥር ከ2 ሺህ 500 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሀገሪቱ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት የአስቸኳይ ጊዜ ከማወጇ በለፈ ጎረቤት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሀገራት እና ተቋማት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርባለች፡፡