በሞሮኮ የአየር ንብረት ለውጥ "አፈታሪክ" ነው የሚሉ አሉባልታዎች እየተሰራጩ ነው
በቅርብ አመታት ውስጥ በሞሮኮ ውስጥ ስለአየር ንብረት ለውጥ "አፈታሪክ" የሚሉ አሉባልታዎች በስፋት ተስፋፍተዋል
አብዛኞቹ የአየር ንብረት ለውጥ የሚባል የለም ብለው የሚስማሙ ሲሆን የባለሙያዎችን የአየር ንብረት ለውጥ ሀሳብ አፈታሪክ እና በመረጃ ያልተደገፈ ነው ሲሉ ይናገራሉ
በቅርብ አመታት ውስጥ በሞሮኮ ውስጥ ስለአየር ንብረት ለውጥ "አፈታሪክ" የሚሉ አሉባልታዎች በስፋት ተስፋፍተዋል፤በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመሰራጨትም ክብረ ወሰን ሰብረዋል።
ነገሩን እንግዳ የሚያደርገው ስለአየር ንብረት የሚያወሩት ሰዎች የአየረ ንብረት ባለሙያዎች፣ የአካባቢ ሳይንቲስቶች ያልሆኑ ሰዎች ነው።
እነዚህ ሰዎች ስለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃ ያሰራጫሉ።
አብዛኞቹ የአየር ንብረት ለውጥ የሚባል የለም ብለው የሚስማሙ ሲሆን የባለሙያዎችን የአየር ንብረት ለውጥ ሀሳብ አፈታሪክ እና በመረጃ ያልተደገፈ ነው ሲሉ ይናገራሉ።
በዚህ ጉዳይ የአካባቢ ጥናት ባለሙያ ቤንራሜል ሙስጣፋ ለአል ዐይን እንደገለጹት የአየር ንብረት ለውጥ አፈታሪክ ነው የሚለውን አጣጥለውታል።
በርናሜል አክለውም "ስለዚህ ጉዳይ ስንሰማ ወይም ስናነብ እና የአየር ንብረት ያመጣውን አደጋ ስንመለከት፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚባል የለም በሚሉ ሳይንቲስቶች እንደተታለልን ይሰማናል" ብለዋል።
አሉባልታዎቹ አእምሮን ለማደንዘዝ ያለሙ ናቸው ያሉት ባለሙያው ምክንያቱን በመቀየር እና ከአየር ንብረት ኃላፊት መሸሽ ትርጉም አልባ ነው ሲሉ ተናግረዋል።