ሞሮኳዊው ታዳጊ ያለፉትን 5 ቀናት ካሳለፈበት ጉድጓድ ወጣ
ያለፉትን 5 ቀናት በድንገት በገባበት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ያሳለፈው የ5 ዓመቱ ታዳጊ ራያን ጉዳይ መላው ዓለምን ሲያነጋግር ነበረ
የሞሮኮ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች 32 ሜትር ጥልቀት ካለው ጉድጓድ ውስጥ የገባውን ታዳጊ በህይወት ለመታደግ ችለዋል
የሞሮኮ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች 32 ሜትር ጥልቀት ካለው ጉድጓድ ውስጥ የገባውን የ5 ዓመቱን ታዳጊ በህይወት ለመታደግ ቻሉ፡፡
አደጋ ጊዜ ባለሙያዎቹ ርያን ይሰኛል የተባለውን ታዳጊ ህይወት ለመታደግ ከሳሰለፍነው ረቡዕ ጀምሮ ከፍተኛ ጥረትን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
በስተመጨረሻም ዛሬ ድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 28 ቀን 2014 ዓ/ም ታዳጊውን ርያንን ገብቶበት ከነበረው 32 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ለማውጣት ችለዋል፡፡
ሴፍሾን በተባለው የሃገሪቱ ክልል በሚገኘው የሰሜናዊ ኢግራም መንደር ነዋሪ የሆነው ርያን ያሳለፍነው ማክሰኞ ነበር በድንገት በወላጆቹ ቤት አቅራቢያ ከሚገኝ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የገባው፡፡
የልጃቸው በድንገት መጥፋት ያሳሰባቸው ወላጆቹ ርያን ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ ጥልቅ ውስጥ መግባቱን ካሳወቁበት ጊዜ ጀምሮም ታዳጊውን በህይወት ለመታደግ የሚያስችሉ እጅግ ፈታኝ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡
የሞሮኮ መንግስትም ታዳጊውን ለመታደግ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹን አሰማርቶ ከፍተኛ ጥረቶችን አድርጓል፡፡
የአፈርና የአለት ቆረጣ ርያንን ርቆ ከገባበት ጉድጓድ ለማውጣት ሲደረጉ የነበሩ ጥረቶች ቀናትን ወስደዋል፡፡ እጅግ ፈታኝም ነበሩ፡፡
ሆኖም በስተመጨረሻ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ታዳጊው ካለበት ስፍራ ለመድረስና በህይወት ለመታደግ ችለዋል፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹን ተከትለው በጥልቀት ወደተቆፈረው ጉድጓድ የዘለቁ የህክምና ባለሙያዎችም አስፈላጊውን ድጋፍ አድርገውለታል፤ ከጉድጓዱ ወጥቶ ወደ ሌላ ቦታ ከመወሰዱ በፊትም መርምረውታል ሌሎች የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታዎችንም አድርገውለታል፡፡
ርያንን በመታደጉ ሂደት ምናልባት ሊገጥሙ የሚችሉ ድንገተኛ አደጋዎች ቢኖሩ እንኳን አስፈላጊውን እርዳታ በቶሎ ለማድረግ የሚያስችሉ ሄሊኮፕተርን ጨምሮ አምቡላንሶች ተዘጋጅተው ነበረ፡፡
ብዙዎችም በዚህ ደስታቸውን በመግለጽና በማጋራት ላይ ይገኛሉ፡፡