ሞሮኮ በአለም ዋንጫው ታሪክ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ለመሆን በቅታለች
የአትላስ አንበሶቹ ለስፔን ላሊጋው ክለብ ሲቪያ የሚጫወተው የሱፍ ነስሪ 42ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ነው ፖርቱጋልን 1 ለ 0 ያሸነፉት።
በዚህም ሞሮኮ በአለም ዋንጫው ታሪክ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሀገር ለመሆን በቅታለች።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተቀይሮ ቢገባም ሀገሩን መታደግ አልቻለም።
በኳታሩ የአለም ዋንጫ እስካሁን አንድ ጎል ብቻ ያስተናገዱት የአትላስ አንበሶቹ፥ 12 ጎሎችን ያስቆጠሩትን ሴሌሳዎቹ በአልቱማማ ስታዲየም ድል አድርገዋል።
ቤልጂየምን ከምድብ ስፔንን ደግሞ ከሩብ ፍጻሜው ውጭ አድርገው ዛሬ ምሽት ደግሞ ፖርቹጋልን ከግማሽ ፍጻሜው አሰናብተዋል።
የአፍሪካ ኩራቶቹ በግማሽ ፍጻሜው ምሽት 4 ስአት ላይ ከሚጫወቱት እንግሊዝ እና ፈረንሳይ አሸናፊ ጋር ይፋለማሉ።