ሩሲያ ማንኛውንም የባህር ስር፣ የባህር ላይ እንዲሁም የአየር ወለድ ጠላቶችን የመለየት አቅም እንዳላት ገልጸዋል
የሩሲያ ባህር ሀይል ማንኛውንም የጠላት ጥቃት የመለየት እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መከላከል የማይቻል ጥቃት መፈጸም እንደሚችል ፕሬዚዳንት ቪላድሚር ፑቲን ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህንን መልእክት ያስተላፉት የብሪታንያ የባህር ሀይል መርከብ የክሬሚያ ሰርጥ ውስጥ ጥሶ በመግባት ሞስኮን ካበሳጨ ከሳምንት በኋላ ነው።
የሩሲያ የባህር ሀይል ቀን በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ በተከበረበት ወቅት ፐሬዚዳንቱ መልእክቱን ማስተላለፋቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን በዚሁ ወቅት “የባህር ስር፣ የባህር ላይ እንዲሁም የአየር ወለድ ጠላቶችን የመለየት አቅም አለን” ሲሉ ተናግረዋል።
“አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜም የተኛውም ሀይል ሊከላከለው የማይችል ጥቃት የመሰንዘር አቅም አለን” ሲሉም ተደምጠዋል።
የብሪታንያ የባህር ሀይል መርከብ ባሳለፍነው ሰኔ ወር የጥቁር ባህር ውስጥ በመታየቱ ሩሲያ በመርከቡ ላይ የማጠንቀቂያ ተኩሶችን ጨምሮ፤ ከክሬሚያ የባህር ክልል እስኪወጣ ድረስ ቦምቦችን በመርከቡ አቅራቢያ መጣሏን መግለጿ ይታወሳል።
ብሪታንያ በበኩሏ ሩሲያ በመርከቡ ላይ ወሰድኩ ያለችውን እርጃ ውሸት ነው በሚል ያጣጣለች ሲሆን፤ በወቅቱ የሩሲያ ባር ሀይል የመሳሪያ ተኩስ ልምምድ እያደረገ እንደነበረ እና በመርከቡ አቅራቢያ የተጣለ ቦምብ እንደሌለም አስታውቃለች።
ሩሲያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 ክሬሚያን በየክሬይን የነጠቀች ቢሆንም፤ ብሪታኒያን ጨምሮ በርካታ የዓለም ሀገራት ግን በጥቁር ባህር ሰርጥ ውስጥ የምትገኘው ክሬሚያ አሁንም የዩክሬን ግዛት እንደሆነአድርገው ነው እውቅና የሚሰጡት።