ፖለቲካ
የሩሲያን ድንበር ሊያቋርጡ የነበሩ የኔቶ ጦር አውፕላኖች በሩሲያ ተጠልፈው መመለሳቸው ተገለጸ
የጦር አውሮፕላኖቹ በጥቁር ባህር በኩል ሲበሩ ነበር ተብሏል
በጥቁር ባህር በኩል የሩሲያን ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የነበሩት የፈረንሳይ እና የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ናቸው ተብሏል
በጥቁር ባህር በኩል የሩሲያን ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የነበሩ የፈረንሳይ እና የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በሱ-27 የሩሲያ ጄቶች ተጠልፈው መመለሳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በፈረንጆቹ ታህሳስ 9 የሩሲያ የኤሮስፔስ መቆጣጠሪያ ሲስተም በራሪ አካላት ወደ ጥቁር ባህርን አልፈው ወደ ሩሲያ ድንበር እየበረሩ እንደሆነ ማመላከታቸውን የሩሲያ ታስ መግለጫውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
እንደ መግለጫው ከሆነ የሩሲያ የኤርክራፍት በረራ ቡድን ወደ ሩሲያ ድንበር አቅጣጫ ሲበሩ የነበሩት ሚራጅ2000 ጀትና ከፈረንሳይ አየርና ስፔስ ሃይል የመጣች የፈረንሳይ ራፋየል ጄት እንዲሁም የአሜሪካ ጦር ሲኤል ያሳተፈ የጥናት እንቅስቃሴ ነበር ተብሏል፡፡
የፈረንሳይ ኬሲ-135 አውሮፕላን ነዳጅ የምትሞላና እጀባ የምታደርግ በጥቁር ባህር ላይ ሲበሩ እንደነበር መግለጫ አመልክቷል፡፡
የጦር ጄቶች አማካኝነት የጦር አውሮፕኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል ያለው መግልጫ የሩሲያ ውጊያ ጄቶች የጦር አውፕላኖቹን ከድንበር ወደ ኋላ ከመለሱ በኋላ በሰላም መመለሳቸው ተዘግቧል፡፡